ዩክሬን እና ሩሲያ የጥቁር ባህሩን የእህል ኤክስፖርት ስምምነት እንዲያራዝሙ ተመድ አሳሰበ
ስምምነቱ የተደረሰው በሩሲያ፣ ቱርክ እና ዩክሬን መካከል ነበር
ከሩሲያ የሚገኘው እህል እና ማዳበሪያም ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ መድረሱን ለማረጋገጥ የተደረሰው ስምምነት እንዲተገበርም አሳስቧል
ተመድ በትናንትናው እለት እንዳሰሰበው በተመድ አመካኝነት ዩክሬን በጥቁር ባህር እህል ወደ ውጭ ኤክስፖርት እንድታደርግ የሚያስችለው ስምምነት እንዲራዘም አሳስቧል፡፡ ስምምነቱ ታድሶ ከህዳር አጋሽ በኋላ መቀጠሉ ለአለም የምግብ ዋስትና አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብሏል፡፡
ከሩሲያ የሚገኘው እህል እና ማዳበሪያም ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ መድረሱን ለማረጋገጥ የተደረሰው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርም አሳስቧል።
የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በሰጡት መግለጫ “ይህንን ማድረጋችን አስቸኳይ የምግብ ዋስትናን ለመላው አለም አስተዋፅኦ ለማድረግ እና ይህ አለም አቀፍ የኑሮ ውድነት በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን እያደረሰ ያለውን ስቃይ ለመቅረፍ አስፈላጊ መሆኑን እናሳስባለን” ብለዋል።
በፈረንጆቹ ሀምሌ 22 በተደረገው ስምምነት ዩክሬን በየካቲት 24 ቀን ሩሲያ ጎረቤቷን በወረረችበት ጊዜ የቆመውን የጥቁር ባህር እህል እና የማዳበሪያ ኤክስፖርት እንደገና መጀመር ችላለች።የዩክሬን ኤክስፖርት ስምምነት መጀመሪያ ላይ ለ120 ቀናት ተስማምቷል።
ተመድ ስምምነቱን ለአንድ አመት ለማራዘም እና በዩኤን፣ ቱርክ፣ ሩሲያ እና የዩክሬን ባለስልጣናት መርከቦች ላይ የጋራ ቁጥጥርን ለማቃለል እየሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡