ፖለቲካ
ሩሲያ በኦደሳ ግዛት በወደብ እና እህል ማከማቻ ላይ ጥቃት አደረሰች
ጥቃት መፈጸሙን በቴሌግራም ገጻቸው የገለጹት የኦደሳ ግዛት አስተዳዳሪ ኦሌህ ኪፐር በሰው ላይ የደረሰ ጥቃት የለም ብለዋል
ሩሲያ ከዚህ ስምምነት የወጣችው ሩሲያን የሚመለከተው የስምምነቱ ክፍል ተግባራዊ አልሆነም በሚል ምክንያት ነው
ሩሲያ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት በኦደሳ ወደብ እና እህል ማከማቻ ላይ ጉዳት አድርሳለች።
ሩሲያ በደቡባዊ ዩክሬን ጠረፍ ላይ በሰነዘረችው የድሮን ጥቃት የእህል ማከማቻዎች እንዲቃጠሉ ማድረጓን ሮይተርስ ዘግቧል።
ጥቃት መፈጸሙን በቴሌግራም ገጻቸው የገለጹት የኦደሳ ግዛት አስተዳዳሪ ኦሌህ ኪፐር በሰው ላይ የደረሰ ጥቃት የለም ብለዋል።
ሩሲያ፣ ዩክሬን እህል ወደ ውጭ ለመላክ ከሚያስችላት "የጥቁር ባህር ስምምነት" ከወጣች በዩክሬን የወደብ መሰረተ ልማቶች ላይ እያደገች ያለውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።
የዩክሬን ሚዲያዎች እንደዘገቡት ከጥቁር ባህር የተነሱት ድሮኖች ለዩክሬን ቁልፍ የሆነውን የኦደሳ ወደብ አጥቅተዋል።
እንደሚዲያዎቹ ዘገባ ከሆነ ስምምነቱ ጊዜ ካለፈበት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ መርከቦች ወደወደቡ ደርሰዋል።
ሩሲያ ከዚህ ስምምነት የወጣችው ሩሲያን የሚመለከተው የስምምነቱ ክፍል ተግባራዊ አልሆነም በሚል ምክንያት ነው።
ሩሲያ ስምምነቱን እንድታድስ እና እህል ወደ አፍሪካ እንዲገባ የአፍሪካ መሪዎች በሴንትፒርስበርግ ጉባኤ ላይ የሩሲያውን ፕሬዝደንት ፑቲንን ጠይቀዋል።