ሩሲያ ወደ ዩክሬን ከተኮሰቻቸው ውስጥ 83ቱ ሚሳኤሎች ከሽፈዋል ተብሏል
ዩክሬን በ93 የሩሲያ ሚሳኤል መጠቃቷን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ተናገሩ፡፡
አንድ ሺህ ቀን ያለፈው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት እንደቀጠለ ሲሆን ኪቭ የሚሳኤለ እና ድሮን ጥቃቶች ስትደበደብ አርፍዳለች ተብሏል፡፡
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ስለ ጥቃቱ በሰጡት አስተያየት ሩሲያ ዩክሬንን በ93 ሚሳኤል እና 300 ድሮኖችን ተጠቅማለች ብለዋል፡፡
ዩክሬን ከምዕራባዊያን ባገኘችው የአየር ጥቃት መቃወሚያ ተጠቅማ 81ቱን ሚሳኤሎች እንዳከሸፈች ፕሬዝዳንቱ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በተለይም ኤፍ-16 የተሰኘው የውጊያ ጀት ከሩሲያ እየተተኮሱ ያሉ ሚሳኤሎችን ለማክሸፍ እንዳገዛት ተገልጿል፡፡
ዩክሬን ከሰሞኑ አሜሪካ ሰራሽ የሆኑ የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማ ሩሲያን ያጠቃች ሲሆን ወታደራዊ ተቋማትን ኢላማ አድርጋለች፡፡
የዛሬው የሩሲያ የሚሳኤል እና ድሮን ጥቃት ለዚህ ኢላማ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን የሀይል እና ትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ኢላማ ተደርገዋል፡፡
በሁለት ግንባር የተሰለፉት ድሮን አዳኝ የተባሉት የዩክሬን ዳኛ
የአሜሪካ ተመራጩ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይህንን ጦርነት በድርድር እንደሚያስቆሙት የተናገሩ ሲሆን ስልጣን ከመረከባቸው በፊት ሩሲያ ከባድ ጥቃት እያደረሰች ትገኛለች፡፡
በአንጻሩ ኔቶ ዩክሬን በዚህ ሰዓት ከሩሲያ ጋር ለድርድር እንዳትቀመጥ ጨና እያደረገ ነው የጠባለ ሲሆን በአንጻሩ አባል ሀገራት ለኪቭ ተጨማሪ የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲያደርጉ እየወተወተ ነው ተብሏል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ዶናልድ ትራምፕ በፓሪስ በተገኙበት ወቅት ከዩክሬን አቻቸው ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጋር ተገናኝተው ጦርነቱ እንዲቆም ግፊት እንዳደረጉ ተገልጾ ነበር፡፡