ሩሲያ ተጨማሪ አምስት ሀገራትን "ወዳጅ ያልሆኑ ሀገራት" ዝርዝር ውስጥ አካተተች
ሩሲያ ወዳጅ ካልሆኑ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ያካተተቻቸው ግሪክን፣ ዴንማርክን፣ ሰሎቬኒያን፣ ክሮሺያን እና ስሎቫኪያን ነው
የዶምባስ ግዛትን ሙሉ በሙሉ ነጻ አወጣለሁ የምትለው ሩሲያ ጦርነቱን አሁንም በደቡብ እና ምሰራቃዊ ዩክሬን ማካሄዷን ቀጥላለች
ሩሲያ አምስት የአውሮፖ ሀገራትን ማለትም ግሪክን፣ ዴንማርክን፣ ሰሎቬኒያን፣ ክሮሺያን እና ስሎቫኪያን ለሩሲያ ወዳጅ አይደሉም ከምትላቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ማካተቷን የሩሲያ መንግስት አስታውቋል።
ሩሲያ በዩክሬን የምታካሂደውን "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" የማይደግፉ በርካታ ሀገራትን ወዳጅ አይደሉም ስትል ፈርጃለች።
"ወዳጅ አይደሉም" ተብለው ጥቁር መዝገብ ውሰጥ የተካተቱት ሀገራት በሩሲያ ያሉ ኢምባሲዎች ወይም ቆንስላቸው ሩሲያዊ ሰራተኛ ለመቅጠር ሲፈልጉ ሙሉ በሙሉ ወይሞ በከፊል እንዳይቀጥሩ እንደሚደረግ ሩሲያ አስታውቃለች።
ሲጅቲኤን እንደዘገበው አሁን ላይ ግሪክ 34፣ ዴንማርክ 20፣ ስሎቫኪያ 16 እንዲቀጥሩ የተፈቀደላቸው ሲሆን ስሎቨናያ እና ክሮሽያ በኢምባሲያቸው ሰው እንዲቀጥሩ አልተፈቀደላቸም።
የሩሲያ ቤተመንግስት ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ እንደተናገሩት ወዳጅ ካልሆኑ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ መካተት ማለት ሀገራቱ ከሩሲዬ ጋር ያላቸው ግንኙነት ይቀንሳል።
ቃል አቀባዩ ወዳጅ ያልሆኑ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ሀገራት በሰው ቅጥር ላይ ከተጣለው እገዳ ውጭ ያለ ቅጣት ስለመኖሩ አልተናገሩም።
ሩሲያ የኔቶ ጦር ወደ ቀድሞ የሶቬት ሀገራት መስፋፋት ለደህንነቷ እንደማያሰጋት በመግለጽ ነበር በዩክሬን ላይ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ያወጀችው።
ከዚህ በተጨማሪም ዩክሬንን ትጥቅ ማስፈታት እና የናዚን አስተሳሰብ ማጥፋት የዘመቻው አላማ መሆኑን ሩሲያ መግለጿ ይታወሳል።
በሩሲያ ርምጃ የተቆጡት ምእራባውያን ሩሲያን ያዳክማል ያሉትን ሁሉ ማእቀብ በሩሲያ ላይ ጥለዋል።
የዶምባስ ግዛትን ሙሉ በሙሉ ነጻ አወጣለሁ የምትለው ሩሲያ ጦርነቱን አሁንም በደቡብ እና ምሰራቃዊ ዩክሬን ማካሄዷን ቀጥላለች።