ዩክሬን በበኩሏ ሩሲያ እስክትወጣ ድረስ እዋጋለሁ ብላለች
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ዩክሬን ሩሲያ የተቆጣጠረችውን ግዛት ማስረከብን ጨምሮ የሞስኮን ሀሳቦች እንድታሟላ ወይም ሰራዊቷ ጉዳዩን እንደሚወስን አስታውቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይህን ያሉት ፕሬዝዳንት ፑቲን ለውይይት በራቸው ክፍት መሆኑን ከተናገሩ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
ዩክሬን እና ምዕራባውያን አጋሮቿ የፑቲንን የእንወያይ ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል ተብሏል።
የሞስኮ ጦር የዩክሬይንን ከተሞች በሚሳይል እና በሮኬት እየደበደበና ሩሲያ የተቆጣጠረችውን የሀገሪቱን አንድ አምስተኛ ክፍል እውቅና እንዲሰጣት መጠየቋ ለጥያቄው ውድቅ መደረግ ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ኪየቭ በበኩሉ ሩሲያ እስክትወጣ ድረስ እዋጋለሁ ብሏል።
የሩሲያ መንግስት የዜና ወኪል እንደዘገበው ላቭሮቭ "የሩሲያን የደህንነት አደጋዎች ለማስወገድ፤አገዛዙን ትጥቅ ማስፈታት እና ከስልጣን ማራገፍ፣ አዲሶቹ መሬቶቻችንን ጨምሮ ሌሎች ሀሳቦችንም ያካትታል።"
"ነጥቡ ቀላል ነው። ለራሳችሁ ጥቅም ስትሉ አሟላላቸው። አለበለዚያ ጉዳዩ በሩሲያ ጦር የሚወሰን ይሆናል" ሲሉ አማራጮችን አስቀምጠዋል።
ፑቲን ዩክሬን ለሩሲያ አስጊ ናት በማለት “ልዩ ተልዕኮ” በማዘዝ ዩክሬንን ከወታደራዊ ነጻ ማድረግን ዓላማ አድርገው ነበር ባለፈው የካቲት ወር ዘመቻ የጀመሩት።
ኪየቭ እና ምዕራባውያን የፑቲን ወረራ የመሬት ነጠቃ ብለውታል።