ሩሲያ በዩክሬን ከተሸነፈች የኑክሌር ጦር መሳሪያዋን እንደምትጠቀም አስጠነቀቀች
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በሞስኮ አሸናፊነት ከተጠናቀቀ ሶስተኛው የዓለም ሊቀሰቀስ ይችላል መባሉ ይታወሳል
የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላው አንድ ወር ብቻ ቀርቶታል
ሩሲያ በዩክሬን ከተሸነፈች የኑክሌር ጦር መሳሪያዋን እንደምትጠቀም አስጠነቀቀች።
ሩሲያ ባሳለፍነው የካቲት ወር ላይ ጦሯን ለጥቂት ቀናት በሚል ለልዩ ዘመቻ ወደ ዩክሬን ብትልክም ጦርነት አንድ ዓመት ሊሞላው ጥቂት ከሁለት ወራት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል።
ጦርነቱ መልኩን እየቀያየረ እና አዳዲስ ክስተቶችን እንዳስመዘገበ የቀጠለ ሲሆን ሩሲያ በዩክሬን ላይ የጀመረችውን ጥቃት አስፋፍታ ቀጥላለች።
በተለይም ዩክሬን ከአሜሪካ እና ምዕራባዊያን ሀገራት በእርዳታ ያገኘቻቸው የጦር መሳሪያዎች በሩሲያ መመታታቸውን ተከትሎ እና የተተኳሽ እጥረት እንደገጠማቸው ተገልጿል።
ሩሲያ በተለይም የአየር ላይ ጥቃቶችን ማስፋቷ ለዩክሬን ጦር አስቸጋሪ ሁኔታን ፈጥሯል የተባለ ሲሆን ምዕራባዊያን ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ እንዲደረጉላት ጠይቃለች።
የሩሲያ የደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሃላፊ ፓቬል ኔድሜዴቭ ሩሲያ በዩክሬን ከተሸነፈች ያሏትን የኑክሌር አረር እንደምትጠቀም ገልጸዋል።
ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የሚያስታጥቁትን የጦር መሳሪያ እንዲያቆሙ ያሳሰቡት ሜድቬዴቭ ሩሲያ ለዩክሬን በተሰጡት የጦር መሳሪያዎች ምክንያት ከተሸነፈች ግን የኑክሌር ጦርነት ይጀመራል ብለዋል።
የኔቶ አባል የሆነችው ፖላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ማቱስዚ ሞራዉኪ ከሰሞኑ እንዳሉት ሩሲያ ዩክሬንን ካሸነፈች ሶስተኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታሰወሳል።
ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እንዳይነሳም ምዕራባዊያን ሀገራት የጦር መሳሪያ ለዩክሬን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠቅላይ ሚንስትሩ አሳስበዋል።
በተለይም ጀርመን ሊዮፓርድ- 2 የተሰኘውን ታንክ የጦር መሳሪያን ለዩክሬን እንድትሰጥ የተጠየቀች ሲሆን ታንኬን ለኬቭ የምሰጠው አሜሪካ ምትክ የምትሰጠኝ ከሆነ ብቻ ነው ስትል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጣለች።
ሩሲያ በበኩሏ የኑክሌር አረር የታጠቁ የባህር፣ የየብስ እና አየር ላይ የጦር አውሮፕላኖቿን ለውጊያ ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረጓን ታስ ዘግቧል።