የሩሲያ የታክቲካል ኑክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ አላማ ምንድን ነው?
ሩሲያ፣ ዩክሬንን በማስታጠቅ እና ጥቃት እንድትከፍት እያደረጉ ነው የሚል ክስ ምዕራባውያንን ታቀርባለች
ሜድቬዴቭ ሩሲያ ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው የአጸፋ ምላሻ በዩክሬን ላይ ብቻ እንደማይወሰን አስጠንቅቀዋል
ሩሲያ በቅርቡ ለማድረግ ያቀደችውን የታክቲካል ኑክሌር ጦር መሳሪያ ጦር መሳሪያ ልምምድ አስፈላጊነትን የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዝደንት እና የሩሲያ የጸጥታ ምክርቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ ግልጽ አድርገዋል።
ሜድቬዴቭ እንዳሉት ሩሲያ ልምምድ የምታደርገው በሩሲያ ምድር ላይ ሊቃጣ የሚችልን ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት የሚያስችል ዝግጅት ለማድረግ ነው።
ሩሲያ፣ ዩክሬንን በማስታጠቅ እና ጥቃት እንድትከፍት እያደረጉ ነው የሚል ክስ ምዕራባውያንን ታቀርባለች።
ሜድቬዴቭ ሩሲያ ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትሰጠው የአጸፋ ምላሻ በዩክሬን ላይ ብቻ እንደማይወሰን አስጠንቅቀዋል።
"ምላሹ ዩክሬን ላይ ብቻ ያነጣጠረ የማይሆንበት ሁኔታ ሊኖር ይችላል" ሲሉ ሜድቬዴቭ በቴሌግራም ገጻቸው ጽፈዋል።
ሞስኮ፣ ከፈረንሳይ፣ ከእንግሊዝ እና አሜሪካ ስጋቶች መኖራቸውን ከገለጸች በኋላ ባለፈው ሰኞ እለት የታክቲካል ኑክሌር ጦር መሳሪያ ልምምድ እንደምታደርግ ገልጻለች።
ሜድቬዴቭ፣ የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በቅርቡ ዩክሬን ከእንግሊዝ የተሰጣትን የጦር መሳሪያ ሩሲያ ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ ተፈቅዶላታል ሲሉ የሰጡትን አስተያየት አንስተዋል።
ሩሲያ በተለይ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከጀመረች በኋላ ዓለም ወደ ኑክሌር ጦርነት ሊገባ ይችላል በማለት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ስታሰማ ቆይያለች።
ምዕራባውያን ወደ ዩክሬን ወታደሮቻቸውን የሚልኩ ከሆነ ከሩሲያ ጋር ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ እንደሚገቡም ፕሬዝደንት ፑቲን ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።
የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን አውሮፓ ወደ ዩክሬን ጦር ሊልክ ይችላል ማለታቸው ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቶ ነበር። ነገርግን የማክሮን ሀሳብ በአውሮፓ ድጋፍ ሳያገኝ ቀርቷል።