ደቡብ ኮሪያ ልዩ ፍቃድ ሳይኖር ወደ ሩሲያ መላክ የለባቸውም ያለቻቸውን እቃዎች ዝርዝር ይፋ አድርጋለች
ሩሲያ፣ ደቡብ ኮሪያ የአጸፋ እርምጃ ቢወሰድባት መገረም የለባትም አለች።
ሩሲያ፣ ደቡብ ኮሪያ በጣለችው ማዕቀብ ምክንያት ሞስኮ የአጸፋ እርምጃ ብትወስድባት መገረም እንደሌለባት ተናግራለች።
ደቡብ ኮሪያ ልዩ ፍቃድ ሳይኖር ወደ ሩሲያ መላክ የለባቸውም ያለቻቸውን እቃዎች ዝርዝር ይፋ አድርጋለች።
ሩሲያን ይህ ውሳኔ አበሳጭቷታል።
ደቡብ ኮሪያ በዚህ ሳምንት ለወታደራዊ አላማ ሊውሉ ይችላሉ ያለቻቸውን 600 የሚሆኑ እቃዎችን ቁጥጥር እንዲደረግባቸው አድርጋለች።
ያለልዩ ፈቃድ ወደ ሩሲያ አይገቡም ከተባሉት መካከል ከባድ የግንባታ ማሽኖች፣ የኤሮኖቲካል ኮምፖኔንትስ እና የተወሰኑ መኪኖች ይገኙበታል።
በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ የሰጡት የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ "ይህ በዋሽንግተን ፍላጎት የተደረገ ተገቢ ያልሆነ እርምጃ ነው። ይህ የራሷን የደቡብ ኮሪያን ኢኮኖሚ እና ኢንዱስትሪ ይጎዳል"ብለዋል።
ማሪያ ዛካሮቫ "በአጸፋዊ እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥበናል፣ ነገርግን አጸፋ እርምጃ ከወሰድን ደቡብ ኮሪያ መገረም የለባትም" ሲሉ ተናግረዋል።
ደቡብ ኮሪያ በቀጣናው የአሜሪካ ዋና አጋር ነች። በዚህ ምክንያት ሩሲያ ደቡብ ኮሪያ የአሜሪካን ፍላጎት ነው ያስፈጸመችው የሚል ክስ አቅርባለች።