“ፑቲን የሩስያ ተቃዋሚ መሪ ናቫልኒ እንዲገደሉ አላዘዙም” -የአሜሪካ ባለስልጣን
የሩሲያ ፖለቲከኛ፣ የፀረሙስና ታጋይና ጠበቃ አሌክሲ ናቫልኒ እስር ቤት ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለናቫልኒ ሞት ፑቲንን ተጠያቂ ማድረጋቸው አይዘነጋም
የአሜሪካ የስለላ ባለስልጣን የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩስያ ተቃዋሚ መሪ ናቫልኒ እንዲገደሉ ትእዛዝ አስተላልፈዋል ብለው እንዳማያምኑ አስታወቁ።
ታዋቂው የሩሲያ ፖለቲከኛ፣ የፀረሙስና ታጋይና ጠበቃ አሌክሲ ናቫልኒ ባሳለፍነው የካቲት ወር እስር ቤት ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ጨምሮ በርካታ ባለስልጣናት ለፖለቲከኛው አሌክሲ ናቫልኒ ሞት ፕሬዝዳንት ቭላሚር ፑቲንን ተጠያቂ ማድረጋቸው አይዘነጋም።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በወቅቱ በሰጡት መግለጫም፤ "አልሳሳትም ለናቫልኒ ሞት ተጠያቂው ፑቲን ነው" ያሉ ሲሆን የ47 አመቱ የፑቲን ዋነኛ ተቃዋሚ እስርና ሞት እንደሚጠብቀው እያወቀ ወደ ሩሲያ መመለሱ የፅናቱ ማሳያ ነው ሲሉ ገልፀዋል።
ሆኖም ግን ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአሜሪካ የስለላ ቢሮ ባለስልጣን ፕሬዝዳንት ፑቲን ፖለቲከኛው አሌክሲ ናቫልኒ በተገደሉበት ወቅት የሚያውቁት ነገር እንዳለ ምንም ማስረጃ አልተገኘም ብለዋል።
የ47ቱ አመቱ ናቫልኒይ ከሞስኮ 1900 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የአርክቲክ እስር ቤት ውስጥ ባሳለፍነው የካቲት ወር ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።
የሩሲያ ባለስልጣናት በወቅቱ በሰጡት በሰጡት መግለጫ፤ ናቫልኒይ በእስር ቤቱ ውስጥ እንቅስቃሴ ካደረገ በኋላ ወዲያውኑ ራሱን ስቶ ህይወቱ ማለፉን መግለጻቸው ይታወሳል።
የናቫልኒ ደጋፊዎች እና ምእራባውያን ታዋቂው የሩሲያ ፖለቲከኛ፣ የፀረሙስና ታጋይና ጠበቃ አሌክሲ ናቫልኒ ተገድሏል የሚል ክስ አቅርበው ነበር።
ክሬሚሊን በናቫልኒይ ሞት ላይ የመንግስት ተሳትፎ የለበትም ሲል ክሱን አስተባብሏል።
የሩሲያ ባለስልጣናት የናቫልኒይን እንቅስቃሴ አክራሪ ሲሉ የፈረጁት ሲሆን ደጋፊዎቹንም በአሜሪካ የሚደገፉ ችግር ፈጣሪዎች ይሏቸዋል።
አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያን ሀገራት ለፕሬዝደንት ፑቲን ዋነኛ ተቀናቃኝ ለሆነው ናቫለኒይ ሞት ፑቲንን ተጠያቂ ማድረጋቸው ይታወሳል።