ፕሬዝደንት ፑቲን የአፍሪካ የሰላም እቅድን ቁልፍ ነጥቦች እንደማይቀበሉ ተናገሩ
የፕሬዝደንት ፑቲን መልስ በኪቭ ተቀባይነት ባጣው እቅድ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል ተብሏል
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ለሚደረግ ንግግር ሩሲያ ከያዘቻቸው የዩክሬን ግዛቶች መውጣት አለባት ሲሉ ተናግረዋል
ፕሬዝደንት ፑቲን፣ የዩክሬን እና ሩሲያን ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረጉ ላሉ የአፍሪካ መሪዎች በሰላም እቅዱ የተካቱት አብዛኞቹ ነጥቦች የተሳሳቱ ናቸው ሲሉ ነግረዋቸዋል።
የፕሬዝደንት ፑቲን መልስ በኪቭ ተቀባይነት ባጣው እቅድ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል ተብሏል።
ኪቭ በደቡባዊ እና በምስራቅ ዩክሬን በኩል ያሉ መሬቶችን ከሩሲያ ለማስለቀቅ ባለፈው ሳምንት መልሶ ማጥቃት ብትጀምርም፣ የአፍሪካ መሪዎች አውነተኛ ስምምነት እንዲደረስ ይፈልጉ ነበር።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ባለፈው አርብ ከመሪዎቹ ጋር ከተሰበሰቡ በኋላ ከሩሲያ ጋር ለሚደረግ ንግግር ሩሲያ ከያዘቻቸው የዩክሬን ግዛቶች መውጣት አለባት ሲሉ ተናግረዋል።
ነገርግን ግዛቶቹን ለቆ በመውጣት ጉዳይ ሩሲያ አትደራደርም።
ፕሬዝደንት ፑቲን በትናንትናው እለት በሴንትፒተርስበርግ ከሴኔጋል፣ ከግብጹ፣ ከኡጋንዳ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ኮሞሮስ እና ደበቡ አፍሪካ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፤ ለአፍሪካ ያላቸውን ድጋፍም ገልጸዋል።
ነገርግን የካሜሩን፣ የሴኔጋል እና ደቡብ አፍሪካ ተወካዮች የሰላም እቁዱን ካቀረቡ በኋላ ፑቲን አለምአቀፍ እውቅና ያለውን ድንበር መቀበል በሚለው የእቅዱን ነጥብ ላይ ጥያቄ አንስተዋል።
ፕሬዝደንቱ ከዩክሬን እና ከምዕራባውያን አጋሮቿ ጋር ጦርነቱ የተጀመረው ሩሲያ ጦሯን ወደ ድንበር ከማሰማራቷ በፊት ነው ብለዋል።
የዓለም የምግብ ዋጋ እንዲጨምር ዋና ምክንያት ምዕራባውያን ናቸው ያሉት ፑቲን ሩሲያ የዩክሬን እህል በጥቁር ባህር በኩል ወደ ውጮ እንዲወጣ ብትፈቅድም አብዛኛው የሚሄደው ወደ ሀብታም ሀገራት ነው ብለዋል።
ሩሲያ ከዩከሬን ጋር የሚደረግ ንግግር አዲስ አውነት እንዲኖር የሚያስችል ወይም ወደ ግዛቷ ያካተተቻቸውን አራት የዩክሬን ግዛቶች የሚቀበል እንዲሆን ትፈልጋለች። ነገርግን ይህ ለዩክሬን ቀይ መስመር ነው።