የሩሲያው ሜድቬዴቭ ዩክሬን ያቀረበችውን የግዛት እንለዋወጥ እቅድ ውድቅ አደረጉ
የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጦርነቱን ለማስቆም ለሩሲያ የግዛት ልውውጥ ጥያቄ ለማቅረብ ማቀዳቸው ተዘግቧል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/12/243-160041-img-20250212-145715-826_700x400.jpg)
ሩሲያ የዩክሬንን 112ሺ ስኩየር ኪሎሜትር የተቆጠጠረች ሲሆን ኪቭ ደግሞ በምዕራብ ሩሲያ በምትገኘው ኩርስክ ግዛት 450 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት ያለው ቦታ ይዛለች
የሩሲያው ሜድቬዴቭ ዩክሬን ያቀረበችውን የግዛት እንለዋወጥ እቅድ ውድቅ አደረጉ።
የኃይለኛው የሩሲያ ጸጥታ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ ዩክሬን ሩሲያ ውስጥ የያችውን ቦታ ሩሲያ በተቆጣጠረችው የዩክሬን ግዛት ለመቀየር ያቀረበችውን ሀሳብ "ትርጉም የለሽ" ሲሉ አጣጥለዋል።
የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጦርነቱን ለማስቆም ለሩሲያ የግዛት ልውውጥ ጥያቄ ለማቅረብ ማቀዳቸውን ሮይተርስ የዘ ጋርዲያን ጋዜጣን ጠቅሶ ዘግቧል።
ከ2008-2012 የሩሲያ ፕሬዝደንት በመሆን ያገለገሉት ሜዳቪዴቭ ሩሲያ ሰላም ማምጣት የሚቻለው በጥንካሬ መሆኑን አሳይታለች ብለዋል። ሩሲያ የዩክሬንን 20 በመቶ ገደማ ወይም 112ሺ ስኩየር ኪሎሜትር የተቆጠጠረች ሲሆን ኪቭ ደግሞ በምዕራብ ሩሲያ በምትገኘው ኩርስክ ግዛት 450 ስኩየር ኪሎሜትር ስፋት ያለው ቦታ ይዛለች።
ዩክሬን ባለፈው ነሐሴ ወር በኩርስክ ግዛት ድንገተኛ ጥቃት የከፈተችው በምስራቅና ደቡብ ዩክሬን የተሰማራው የሩሲያ ኃይል ወደ ኋላ ያፈገፍጋል በሚል ስሌት ነበር። ነገርግን የሩሲያ ኃይሎች ጦርነቱ ሲጀመር ከነበረው ፍጥነት ጋር በሚመሳሰል መልኩ በርካታ የዩክሬን መንደሮችን መቆጣጠር ችለዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሶስት አመት አመት ሊሞላው ሁለት ሳምንት ገደማ የቀረውን የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ለማስቆም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውንና መሻሻሎች መኖራቸውንም ተናግረዋል። ትራምፕ በቅርቡ ጦርነቱ በሚቆምበት ሁኔታ ከሩሲያው ፕሬዝደንት ፑቲን ጋር በስልክ መናገራቸው ይፋ አድርገዋል። ሩሲያ ግን መሪዎቹ መነጋገራቸው ማረጋገጥም ሆነ ማስተባበል እንደማትፈልግ ገልጻለች።