ፌስቡክን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የሚከታተል ልዩ ማእከል መክፈቱን አስታውቋል
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ፌስቡክ በሀገሪቱ የዜና ማሰራጫዎች ላይ በያዘው አቋም ምክንያት ገደብ እንደጣለችበት አስታወቀች።
የሩሲያ የኮሙዩኒኬሽን ተቆጣጣሪ ተቋም ሮስኮመናደዞር እንዳስታወቀው ፌስቡክ በመገናኛ ብዙሃን ላይ እያዳረገ ባለው ሳንሱር የሩሲያ ዜጎችን መብት እና ነጻነት ተጋፍተዋል በሚል ይከሳል።
ፌስቡክ በበኩሉ በሩሲያ መንግስት ባለቤትነት የሚተዳደሩ የዜና ድርጅቶች የሚወጡ መረጃዎችን መፈተሽ እና መለየት ለማቆም ፈቃደኛ ሳይሆን መቆየቱን አስታውቋል።
ፌስቡክ በሩሲያ መንግስት ባለቤትነት የሚተዳደሩ የዜና ድርጅቶች ላይ ሳንሱር ማድረግ የጀመረው ሩሲያ በዩክረን ወታደራዊ ዘመቻ ማድረግ መጀመሯን ተከትሎ እንደሆነ አስታውቋል።
ሩሲያም ይህንን ተከትሎ ፌስቡክ ላይ ገደብ የጣለች ሲሆን፤ ገደቡ ምን ያክል ነው የሚለው እና ሌሎች በሜታ ኩባንያ ስር የሚስሩ እነ ዋትሳፕ፣ ፌስቡክ ሜሴንጀር እና እንስታግራምን ስለ ማካተቱ በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም።
የሩሲያ የኮሙዩኒኬሽን ተቆጣጣሪ ተቋም ፌስቡክ ከሳላፈነው ሀሙስ ጀምሮ በሩሲያ መንግስት ባለቤትነት የሚተዳደሩ የዜና ተቋት ማለትም አር.አይ.ኤ፣ ዛቬዝዳ ተሌቪዥና ጣቢያ፣ ሌንታ.አር.ዩ እና ጋዜጣ አር.ዩ ላይ ያስቀመጠውን ተቋም እንዲነሳ ጠይቋል።
ሆኖም ግን ፌስቡክን የሚያስተተዳድረው ሜታ ኩባኔጣ የቀረበለትን ጥያቄ ሳይቀበል መቅረቱን ነው ተቆጣጣሪ ተቋሙ ያስታወቀው።
የሜታ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ምክትል ስራ አስኪያጅ ሰር ኒክ ከሌጅ፤ “የሩሲያ ባለስልጣናት በሩሲያ የዜና ድርጅቶች ላይ የምናደርገውን የማጣራት፣ መፈተሽ እና መለየት ስራ እንድናቆም አዘውናል፤ እኛ ግን አልተቀበልነውም” ብለዋል።
ሆኖም ግን “ሩሲያውያን ፌስቡክን ጨምሮ ሌሎችም የሜታ አገልግሎቶችን መጠቀም እንደሚችሉ ገልጽ አድርገናል” ያሉት ስራ አስኪያጁ፤ “ሩሲያውያን መተግባሪያዎቻችንን መጠቀምን ቀጥለዋል፤ እኛም ድምጻቸው እንዲሰማ ማድረግ እንቀጥላለን” ብለዋል።
ፌስቡክን የሚያስተዳድረው ሜታ ካሳለፍነው ሀሙስ ጀምሮ በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት የሚከታተል ልዩ ማእከል መክፈቱን አስታውቆ ነበር።