የሩሲያ ፓርላማ ዶኔትስክ፣ ሉንሃስክ፣ ዛፖሪዝያና ኬህርሶን ክልሎች የሩሲያ ፌዴሬሽን አካል አድርጎ ተቀበለ
የዩክሬኖቹ ዶኔትስክ፣ ሉንሃስክ፣ ዛፖሪዝያና ኬህርሶን ክልሎች ባሳለፍነው አርብ ከሩሲያ ጋር በይፋ ተዋህደዋል
የሩሲያ የህግ አውጭዎች ክልሎች የሩስያ ፌዴሬሽን አካል መሆናቸውን አስመልክቶ ህገ መንግሰታዊ ውሳኔን አጽድቀዋል
የሩሲያ ፓርላማ (ዱማ)ዶኔትስክ፣ ሉንሃስክ፣ ዛፖሪዝያና ኬህርሶን ክልሎች የሩሲያ ፌዴሬሽን አካል አድርጎ በይፋ ተቀበለ።
የዩክሬኖቹ ዶኔትስክ፣ ሉንሃስክ፣ ዛፖሪዝያና ኬህርሶን ክልሎች ባሳለፍነው አርብ ከሩሲያ ጋር በይፋ መዋሃደቸውን የሚያመላክት የፊርማ ስነ ስርዓት መካሄዱ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም የሩሲያ ፓርላማ (ዱማ) በዛሬው እለት የተሰበሰበ ሲሆን፤ ዶኔትስክ፣ ሉንሃስክ፣ ዛፖሪዝያና ኬህርሶን ክልሎች ከሩሲያ ጋር በይፋ መዋሃዳቸውን አስመልክቶ የተፈረመውን ስምምነት ተቀብሎ አጽድቋል
በዚህም መሰረት ዶኔትስክ፣ ሉንሃስክ፣ ዛፖሪዝያና ኬህርሶን ክልሎች የሩሲያ ፌዴሬሽን እንድ አካል እድርጎ መቀበሉን ዱማው አረጋግጧል።
በተጨማሪም የሩሲያ የህግ አውጭዎች ክልሎች የሩስያ ፌዴሬሽን አካል መሆናቸውን አስመልክቶ ህገ መንግሰታዊ ውሳኔን ማጽደቃቸውን አር.ቲ ዘግቧል።
በአዲሱ ህግ መሰረትም በአራቱ ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ ሁሉም ሰዎች የሩሲያ ዜግነትን እንዲያገኙ የሚፈቅድ ሲሆን፤ መቀበል የማይፈልጉ ሰዎችም መብታው ይጠበቃል ተብሏል።
ሩሲያ፤ በዩክሬን ስር የነበሩ እና ባሳለፍነው ሳምንተ በህዝበ ውሳኔ ሩሲያን ለመቀላቀል የወሰኑ አራት ክልሎችን ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ወደ ግዛቷ በይፋ ጠቀለለች።
ዶኔትስክ፣ ሉንሃስክ፣ ዛፖሪዝያ እና ኬህርሶን የሩሲያ ፌዴሬሽን አንድ አካል መሆናቸውን ፕሬዝዳንት ፑቲን በፊርማቸው አጽደቀዋል።
የዩክሬን ግዛት የነበሩት ሉሃንስ፣ኬርሰን፣ ዛፖሮዚየ እና ዶንቴስክ ክልል መሪዎች በተገኙበት የሩሲያ አካል መሆናቸው በይፋ መታወጁም ይታወሳል።
በዩክሬን እንዲሁም በበርካታ የምዕራባውያን ሀገራት ውግዘት የደረሰበት ህዝብ ውሳኔ ከመስከረም 13 ስከ መስከረም 17 ድረስ በሩሲያ በተያዙ ግዛቶች መካሄዱ ይታወሳል።
ህዝበ ውሳኔው የተካሄደው በአራት የዩክሬን ግዛቶች ላይ ሲሆን፤ ሉሃንስክ እና ዶኔትስክ ሪፐብሊኮች ያካተተ ነበር።
የህዝበ ውሳኔው ድምጽ አሰጣጥ መጠናቀቁን ተከትሎ በተካሄደው ቆጠራም 96 በመቶ ዩክሬናውያን ሩሲያን ለመቀላቀል መወሰናቸውን የሞስኮ ደጋፊ ባለስልጣናት ገልጸዋል።