ሞስኮ፣ በዩክሬን በውጊያ ቀጣና ውስጥ የነበሩ 700ሺ ህጻናት ሩሲያ ውስጥ መሆናቸውን ገለጸች
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንደቀጠለ ነው
ዩክሬን ሩሲያ ህጻናት በህገወጥ መልኩ ከቤታቸው እንዲሰደዱ አድርጋለች የሚል ክስ እያሰማች ነው
የሩሲያ ፌደሬሽን ምክርቤት የአለምአቀፍ ኮሚቴ ኃላፊ የሆኑት ግሪጎሪ ካራሲን ባለፈው እሁድ እንደተናገሩት ሩሲያ በውጊያ ቀጣና የነበሩትን 700ሺ ህጻናት ወደ ግዛቷ አምጥታለች ብለዋል።
ካራሲን በቴሌግራም በጻፉት መልእክት 700ሺ ህጻናት ጦርነት ሸሽተው ከኛ ጋር ተጠልለዋል ሲሉ ተናግረዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተችው በፈረንጆቹ የካቲት 2022 ነበር።
ሩሲያ ህጻናትን ከዩክሬን ወደ ግዛቷ ያመጣችው ወላጅ አልባ እና የተጣሉ ህጻናት እንዳይጎዱ በማሰብ ነው በማለት እርምጃ ትክክለኛ መሆኑን ገልጻለች።
ነገርግን ዩክሬን ህጻናት በህገወጥ መልኩ ከቤታቸው እንዲሰደዱ አድርጋለች የሚል ክስ እያሰማች ነው። አሜሪካም በተመሳሳይ የሩሲያን ምክንያት አትቀበልም።
የህዝብ እና የህጻናት እንቅስቃሴው በሰፊው የታየው ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ በነበሩ ጥቂት ወራት ውስጥ ነው።
በነሐሴ ወር መጨረሻ ዩክሬን መልሶ ማጥቃት በመክፈት በምስራቅ እና በደቡብ ግንባር ብዙ ቦታዎችን ማስለቀቅ ችላ ነበር።
የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንደቀጠለ ነው።