የዩክሬን መጠነ ሰፊ የድሮን ጠቃት በሞስኮ የአውሮፐላን በረራዎችን አስተጓግሎ ነበር
ሩሲያ ዩክሬን በሞስኮ ላይ ልትፈፅም የነበረ መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ማከሸን አስታወቀች።
የሩሲያ ጦር በዛሬው እለት እንዳስታወቀው በሞስኮ ከተማ ላይ ጥቃት ሊፈጽሙ የነበሩ 20 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) መትቶ ጥሏል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳለው፤ የዩክሬን ድሮኖች ተመትተው የወደቁት ከሞስኮ በተጨማሪ፣ በቱላ፣ ከሉጋ እና ብራይንስክ ክልሎች ነው።
በቱላ ክልል ድሮኑ በአየር ላይ በሚመተበት ወቅት በመኖሪያ ህንጻ (አፓርትመንት) ላይ ወደቆ አንድ ሰው መጎዳቱን የክልሉ አስተዳዳሪ አሌከሲ ዳዩሚን አሰታውቀዋል።
- ዘለንስኪ ዩክሬንያውያን ሩሲያ በክረምት ለምትከተፍተው ጥቃት እንዲዘጋጁ አሳሰቡ
- በሩሲያ በኩል ያሉ የኑክሌር ማስፈራሪያዎች ለምዕራባውያን "የመጨረሻ ጥሪ" ናቸው ተባለ
የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጊ ሶባይን በበኩላቸው፤ በሞስክ ላይ ሌሊቱን በርካታ የድሮን ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
ዘ ኮመርሳት የተባለ የሩሲያ ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ በዩክሬን የድሮን ጥቃቶች ምክንያ በሞስኮ ዋነኛው አውሮፕላን ማረፊያ የአውሮፕላን በረራዎች መዘግየታቸውን እና መሰረዛቸውን አስታውቋል።
ዩክሬን በሞስኮ እና በሌሎች የሩሲያ አካባቢዎች ላይ ስለፈጸመችው የድሮን ጥቃት እስካሁን ያለችው ነገር የለም።
ሩሲያ በትናትናው እለት የዩክሬኗ ኪቭ ከተማን በ75 ድሮን መደብደቧን የዩክሬን ባለስልጣናት መናገራቸወ ይታወሳል።
የዩክሬን ባለስልጣናት ሩሲያ አድርሳዋለች ባሉት ከባድ የድሮን ጥቃት አምስት ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ተብሏል።
ቅዳሜ ጠዋት የተጀመረው ጥቃት የኪቭ ከተማ የተለያዩ ክፍሎችን ማጥቃቱን ሮይተርስ ዘግቧል። የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደወሉ ለስድስት ሰአታት ሲሰማ ቆይቶ እንደነበረም ተገልጿል።
የዩክሬን አየር ኃይል ጥቃት ከሰነዘሩት 75 ድሮኖች ውስጥ 74ቱን ምትቼ ጥያለሁ ብሏል። ሩሲያ በጉዳይ ላይ ያለችው ነገር የለም።