የክሬምሊን ቃል አቀባይ የተፎካካሪዎች “በጸረ-ሩሲያ የተተበተበ ንግግር” በብሪታኒያ መሪዎች ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎናል ብለዋል
ሩሲያ በተሰተናባቹ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከስልጣን መልቀቅ ደሰተኛ መሆኗ ብትገልጽም፤ከአዲሷ የብሪታኒያ መሪ “ብዙም የተለየና አውንታዊ ነገር” እንደማትጠብቅ ገለጸች፡፡
ሊዝ ትረስ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመርጠዋል፡፡
ሊዝ ትረስ የቀድሞውን የፋይናንስ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክን በማሸነፍ የብሪታያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡
ሊዝ ትሩስ የብሪታኒያው የወግ አጥባቂ ገዥ ፓርቲ እና የሚቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትር መሪ ሆነው ይመረጣሉ የሚል ግምት አግኝተው ነበር፡፡
ሊዝ ትረስ ቦሪስ ጆንሰንን በመተካት የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዋል፡፡
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ለብሪታኒያ መሪነት እየተወዳደሩ ከሚገኙ እጩዋች የሚደመጠው “በጸረ-ሩሲያ የተተበተበ ንግግር” ሩሲያ በብሪታኒያ መሪዎች ላይ ተስፋ እንድትቆርጥ አድርጓታል ማለታቸውም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
"አዎንታዊ ነገር ተስፋ የምናደርግ አይመስለኝም” ብለዋል ቃል አቀበዩ፡፡
የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለወራት የቆየውን አሉባልታ ተከትሎ ነበር ስልጣን እንደሚለቁ ያስታወቁት፡፡
አሸናፊዋ ሊዝ ትረስ ወደ ስኮትላንድ በመሄድ ንግስቲቱን ያገኛል፡፡
ትረስ ከ2015 ምርጫ በኋላ የኮንሰርቫቲቭስ አራተኛው ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን ችለዋል፡፡ በዚያ ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱ ከቀውስ ወደ ቀውስ ስትሸጋገር የቆየች ሲሆን በሐምሌ ወር 10 ነጥብ1 በመቶ በሆነው የዋጋ ግሽበት ሳቢያ የረዥም የኢኮኖሚ ውድቀት ነው ተብሎ የሚገመተው።
የ47 ዓመቷ የጆንሰን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትረስ የብሪታንያ የኑሮ ውድነት ችግርን ለመቅረፍ በፍጥነት እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገብተዋል፡፡