የሩሲያ ጦር የኪቭ ከተማ በሶስት አቅጣጫ መክበቡን አስታውቀዋል
ሩሲያ ጦር ከ3 ሺህ በላይ የዩክሬን የጦር መሰረተ ልማችን ማውደሙን አስታውቋል።
የሩሲያ ዪክሬን ጦርነት ከተጀመረ ዛሬ 18ኛ ቀኑን መያዙ የሚታወቅ ሲሆን፤ የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን በኩል አዳዲስ አካባቢዎችን እየየዘ መሆኑ ታውቋል።
በዛሬው እለትም የሩሲያ አየር ኃይል በምእራብ ዩክሬን የሚገኝ ወታደራዊ የዩክሬን ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ ላይ የአየር ድብደባ መፈፀሙ ተነግሯል።
የሩሲያ የዜና ኤጀንሲ የሀገሪቱን መከላከያ ሚኒስትር ዋቢ በማድረግ ባወጣው ዘገባውም፤ የሩሲያ ጦር እስካሁን 3 ሺህ 687 የዩክሬን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን አውድሟል።
በአሁኑ ወቅትም የሩሲያ ጦር ወደ ዩክሬኗ ኪቭ ከተማ እየተጠጋ ሲሆን፤ ጦሩ በበቫስሊኪይ ከተማ በመስተምእራብ የሚገኝ አውሮፕላን ማረፊያ ማውደሙም ታውቋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት አማካሪ መይክሃሊዮ ፖዶለያክ፤ ኬቭ እስካሁን መደበኛ ስራዋን ቀጥላች ያሉ ሲሆን፤ በሩሲያ ከበባ ውስጥ የምትገኘው ከተማዋን ለመጠበቅ የዩክሬን ጦር እና በጎ ፍቃደኛ ተዋጊዎች በዝግጅት ላይ ናቸው ብለዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘሌንስኪ በበኩላቸው፤ ሩሲያ ኪቭ ከተማን ለመቆጣጠር ከሞከረች ከፍተኛ ውድመት ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስታውቀዋል።