ሩሲያ የዩክሬን የኢንዱስትሪ ማእከል የሆኑትን በዶንባስ ግዛት የሚገኙ ቁልፍ የኢንዱስትሪ ከተሞችን ለመቆጣጠር ጦርነት እያካሄደች ነው
የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ እንደተናገሩት ዶምባስ ግዛትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ነጻ ማውጣት ሩሲያ ቅድሚያ የምትሰጠው ተግባር ነው፤ ሌሎች የዩክሬን ግዛቶች እጣፋንታቸውን በራሳቸው ይወስናሉ ብለዋል፡፡
ላቭሮቭ ይህን ያሉት ከፈረንሳዩ ቲኤፍ1 ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት ሩሲያ የዩክሬን የኢንዱስትሪ ቦታዎች በሆኑትና እና በዶንባስ ግዛት በሚገኙ ሁለት ቁልፍ ከተሞች ላይ የሚያርጉትን ጥቃት አጠናክረው ቀጥለውዋል፡፡ ዶንባስ ግዛት ዶንቴክስን እና ሉሃንስክ ግዛትን ይይዛል፡፡
የሩሲያ ኃይሎች በሉሃንስክ የምትገኘውን ሰቭሮ ዶኔስክን ከተማ ለመቆጣጠር ጥቃት አጠናክረው መቀጠላቸውን የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ተናግረዋል፡፡
በሩሲያ እውቅና የተሰጣቸው ዶንቴክስና እና ሉሃንስክ ግዛቶች ነጻ መውጣት ለድርድር የሚቀርብ አይደለም ሲሉ ላቭሮቭ መናገራቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ሌሎች የዩክሬን ግዛቶች፣ሩሲያ ጠል በሆነው እና በኒዮ ናዚ ግዛት ውስጥ ይቆያሉ ብለው እንደማያምኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ በዩክሬን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ ያደረገችው” ጎረቤቷን ዩክሬንን ትጥቅ ለማስፈታት እና የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ ወደ ምስራቅ የሚያደርገውን መስፋፋት ለማስቆም ነው፡፡ ነገርግን ዩክሬን በዚህ ሀሳብ አትስማማም፡፡
ሩሲያ "ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ስትል የገለጸችውን በየካቲት 24 በዩክሬን ለ"ዶኔትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ" እና "የሉሃንስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ" በዩክሬን ምስራቃዊ ዩክሬን እንደ ገለልተኛ እና ሉዓላዊ መንግስታት እውቅና መስጠቱን ተከትሎ ነበር፡፡
አሜሪካን ጨምሮ ምእራባውያ ሩሲያን ያዳክማል ያሉትም ማእቀብ ሁሉ ጥለውባታል፡፡ ሩሲያ በበኩሏ ምእራባውያንን ነዳጇን በሩብል እንዲገዙ በማድረግ ለመበቀል ጥራለች፡፡