የሩሲያ ጦር ሴቪየርዶኔትስክ የተባለች ቁልፍ ከተማ እየተቆጣጠሩ መሆኑን ዩክሬን አስታወቀች
ዩክሬኗ ሉሃንስክ ግዛት አስተዳዳሪ፤ የሩሲያ ጦር ወደ ሴቪየርዶኔትስክ ከተማ ዘልቆ እየገባ ነው ብለዋል
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በከተማዋ የሚገኙ መሰረተ ልማቶችና ህንጻዎች 90 በመቶ ወድመዋል ብለዋል
የሩሲያ ጦር በዩክሬኗ ሉሃንስክ ክልል ውስጥ የምትገኝ ቄልፍ ከተማ መቆጣጠራቸው ተገለፀ።
ሉሃንስክ ግዛት አስተዳዳሪ ሴሪ ሃይዳይ፤ ሴቪየርዶኔትስክ ከተማ ዙሪያ ላይ የነበረው የሩሲያ ጦር ወደ ከተማዋ ዘልቆ እየገባ እና እየተቆጣጠረ መሆኑን አስታውቀዋል።
አስተዳዳሪው ሴሪ ሃይዳይ ለዩክሬን ብሄራዊ ቴሌቪዥና ጣያ በሰጡት መግለጫ፤ “ዛሬ የሚያሳዝን ዜና ነው ይዘን የቀረብነው፤ ጠላት ወደ ሴቪየርዶኔትስክ ከተማ ዘልቆ እየተገባ ነው” ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት በሴቪየርዶኔትስክ ከተማ የጋዝ እና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሌላ ያስታወቁት ዋና አስተዳዳው፤ እነዚህን አገልግሎቶች መመለስ አዳጋች መሆኑንም ገልጸዋል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ በበኩላቸው፤ በሴቪየርዶኔትስክ ከተማ የሚገኙ ወሳኝ መሰረት ልማቶች ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን እና በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ህንጻች 90 በመቶው መውደማቸውን አስታውቀዋል።
የምዕራቡ ዓለም የወታደራዊ ሳይንስ ልሂቃን፤ በሴቪየርዶኔትስክ እና ሊይሲቻንስክ የሚደረግ ጦርነት ባለፈው ሳምንት በሩሲያ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ከወደቀችው ማሪዩፖል ከተማ ቀጥሎ የሚደረግና በጦርነቱ ምናልባትም የሩሲያ የበላይነት የሚታይበት ሊሆን የሚችል ነው ብለዋል።
ዩክሬን የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ከጀመረች ሶስት ወራት አልፎታል።
በዚህ ጦርነት ምክንያት የዩክሬን ዋና ዋና የሚባሉ ከተሞችን ጨምሮ የንግድ ማሳለጫ ወደቦች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች መውደማቸውም ይታወቃል።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሜር ዘሌንስኪ ከቀናት በፊት ባሰሙት ንግግር፤ በዩክሬን እየተካሄደ ያለው "ትርጉም-አልባ ጦርነት" እንዲያበቃ ምእራባውያን ከሩሲያ ጋር የገቡትን አላስፈላጊ ጨዋታ ሊያቆሙ ይገባል ብለዋል።