ሩሲያ በጥቁር ባህር ኮሪደር የሚደረግ የመርከብ ጉዞ “ተቀባይነት የለውም” አለች
ሚኒስትሩ መርከቦች በኮሪደሩ ማለፋቸውን ከቀጠሉ ስለሚውደው እርምጃ ያለው ነገር የለም
ባለፈው ሰኞ 354ሺ በላይ የግብርና ምርቶችን የጫኑ መርከቦች ከዩክሬን ወደቦች ተንቀሳቅሰዋል
ሩሲያ በጥቁር ባህር ኮሪደር የሚደረግ የመርከብ ጉዞ ተቀባይነት እንደሌለው በትናንትናው እለት አስታውቃለች፡፡
ሩሲያ ይህን ያለችው ዩክሬን በጥቁር ባህር በኩል እህል በድጋሚ ወደ ውጭ እንድትልክ ካስቻለው በተመድ እና በቱርክ አማካኝነት ተደርሶ ከነበረው ስምምነት ራሷን ማግለሏን ማሳወቋን ተከትሎ ነው፡፡
ከወራት በፊት ሩሲያ በዩከሬን ላይ የጀመረችውን ወታደራዊ ጥቃት ተከትሎ የተቋረጠውን የዩክሬን እህል ወደ ውጭ የመላክ ስራ፣ ተመድ እና ቱርክ ባደረጉት ጥረት ዩክሬን በጥቁር ባህር ወደ ውጭ እንድትልክ ሩሲያ ተስማምታ ነበር፡፡
ነገርግን ሩሲያ ዩክሬን መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደከፈተችባት መግለጽ ስምምነቱ እንዳይራዘም እና በስምምነቱ እንደማትገዛ መግለጿ ይታወሳል፡፡
የዩክሬን አመራሮች እና የአየር ኃይል አዛዦች የመርከቦቹን መንቀሳቀስ በሩሲያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት ለመሰነዘር ስለሚጠቀሙበት በኮሪደሩ የመርከቦቸ እንቅሰቃሴ ተቀባይነት እንደሌለው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ዩክሬን በኮሪደሩ ምንም አይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንደማታደርግ ካልተስማማች በኮሪደሩ ምንም አይነት የደህንነት ዋስትና አይኖርም ብሏል፡፡
ሩሲያ ከስምምነቱ አለመውጣቷን እና እንዲታገድ ማድረጓን ገልጿል ሚኒስቴሩ፡፡ ሚኒስትሩ መርከቦች በኮሪደሩ ማለፋቸውን ከቀጠሉ ስለሚውደው እርምጃ ያለው ነገር የለም፡፡
ባለፈው ሰኞ በጣም ከፍተኛ ነው የተባለ 354ሺ በላይ የግብርና ምርቶችን የጫኑ መርከቦች ከዩክሬን ወደቦች ተንቀሳቅሰዋል፡፡