ሩሲያ፤ የዩክሬን አመራር የሩሲያን ፍላጎቶች በማሟላት “መከራን ማስቆም” ይችላል አለች
ሩሲያ የምእራባውያን ወታደራዊ ጥምረት ወደ ቀድሞ ሶቬት ሀገራት እየተስፋፋ ነው በሚል ነበር ጦርነት የተከፈተችው
ሩሲያ በዩክሬን የኤሌክትሪክ አውታር ላይ ያደረሰችውን ጥቃት በሲቪሎች ላይ ያነጣጠረ ነው የሚለውን ክስ አትቀበልም
ሩሲያ በዩክሬን የኤሌክትሪክ አውታር ላይ ያደረሰችውን ጥቃት በሲቪሎች ላይ ያነጣጠረ ነው የሚለውን ክስ አትቀበልም፡፡
ነገር ግን ኪየቭ ግጭቱን ለመፍታት የሩሲያን ፍላጎት በማሟላት የህዝቡን ስቃይ ማስቆም ትችላች ብሏል።
ባለፉ ሳምንታት በዩክሬን በሚገኙ የሃይል መሠረተ ልማቶች ላይ ተደጋጋሚ በተፈጸመ የሚሳይል ጥቃት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለሰዓታት ወይም ለቀናት ያለ ብርሃን እና ውሃ ወይም ማሞቂያ እንዲጠፉ አስገድዷቸዋል፡፡
ነገር ግን የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ እንደተናገሩት ማህበራዊ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ላይ ኢላማ ያደረገ ጥቃት አለመሰንዘሩን ተናግረዋል፡፡
"ከወታደራዊ አቅም ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የተያዙ ኢላማዎችን በተመለከተ፣ በዚህ መሰረት ጥቃት ይደርስባቸዋል" ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡
ፔስኮቭ በዩክሬን ሲቪሎች ላይ የሚደርሰው ስቃይ ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቋም ጋር እንዴት ሊታረቅ እንደሚችል ተጠይቀው ነበር። ፑቲን ሩሲያ ዩክሬንን እና ህዝቦቿን ለመጉዳት እንደማትፈልግ ተናግረዋል፡፡
"የዩክሬን አመራር ሁኔታውን ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ ሁሉም እድል አለ፤ የሩስያ ጎን መስፈርቶችን ለማሟላት እና በዚህ መሠረት በህዝቡ መካከል ሊደርስ የሚችለውን ስቃይ ለማስቆም በሚያስችል መልኩ ሁኔታውን ለመፍታት እድሉ አለው" ሲል ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡
ሩሲያ የምእራባውያን ወታደራዊ ጥምረት ወደ ቀድሞ ሶቬት ሀገራት እየተስፋፋ ነው በሚል በዩክሬን የጀመረችው ጦርነት እስካሁን አልተቋጨም፡፡