የዩክሬን ፕሬዝዳንት ሩሲያ “ሽብር እና ግድያ” ጀምራለች ሲሉ ከሰሱ
ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ "ጠላት በሀገራችን ላይ ላደረሰው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል" ብለዋል
የሩሲያ ኃይሎች በሆስፒታል ላይ ባደረሱት ጥቃት “አዲስ የተወለደ ህጻን” መገደሉ ተገልጿል
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ድል የራቃት ሩሲያ 'ሽብር እና ግድያ' ጀምራልች ሲሉ ከሰሱ
ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በደቡብ ዛፖሪዝሂያ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል የእናቶች ክፍል ላይ የሩሲያ ኃይሎች ባደረሱት ጥቃት አዲስ የተወለደ ህጻን መገደሉን ተከትሎ ነው፡፡
ረቡዕ ምሽት ላይ በዛፖሪዝሂሂያ ክልል ውስጥ በቪልኒያንስክ ከተማ ውስጥ በአካባቢው ሆስፒታል ግዛት ላይ በተሰነዘረው የሮኬት ጥቃት ምክንያት የወሊድ ክፍል የሆነው ባለ ሁለት ፎቅ ህንጻ መውደሙ ኤኤፍፒ የነፍስ አድን ሰራተኞችን ጠቅሶ ዘግቧል ፡፡
በህንጻው ውስጥ "አንድ አራስ ልጅ ይዛ ምጥ ላይ ያለች ሴት እንዲሁም ዶክተር" እንደነበሩም ጭምር ተናግረዋል፡፡
"በጥቃቱ ምክንያት እንደፈረንጆቹ በ 2022 የተወለደ ህጻን ሞቷል ፣ ሴትዮዋ እና ሀኪሟ ከፍርስራሹ ውስጥ ተገኝተዋል"ም ብለዋል የነፍስ አድን ሰራተኞቹ፡፡
በሰራተኞቹ የተለቀቀው ቪደዮ የሚያሳየውም የእናቶች ማቆያ በሚመስለው ፍርስራሽ ውስጥ ወገብ ላይ የተቀረቀረ ሰው ለማስወጣት ጥረት ሲደረግ ነው፡፡
በሁኔታው እጅጉን ያዘኑት ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ በማህበራዊ አውታረ መረቦች ላይ "ጠላት ለዘጠኝ ወራት ሊያሳካው ያልቻለውን እና ሊያሳካው የማይችለውን ነገር በሽብር እና በመግደል ለመሞከር እንደገና ወስኗል" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
"ይልቁንስ በሀገራችን ላይ ላደረሰው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል" ሲሉም አክለዋል ዘሌንስሊ።
ዩክሬን ይህን ተበል እንጅ በሩስያ በኩል ድርጊት ስለመፈጸሟ አስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡