ሩሲያ የመድፍ ተተኳሽ እጥረት እንደገጠማት የአሜሪካ መከላከያ አዛዥ ተናገሩ
ለ9 ወራት በዘለቀው የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት የሞስኮ የመሣሪያዎች አቅርቦት "በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል" ብለዋል
ኪየቭ የሞስኮን የጥይት ማከማቻ ቦታዎችን መምታቷ የሩሲያውያን የጥይት አቅም እንዲወርድ አድርጓልም ተብሏል
የዩናይትድ ስቴት የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን የሩሲያ ጦር ኃይሎች በዩክሬን ውስጥ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ የሚያዳክም “ከፍተኛ” ጥይቶች እጥረት እየተሰቃዩ ነው ብለዋል።
ሚንስትሩ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “ሩሲያውያን በዩክሬን ጦርነት ከጅምሩ ጀምሮሩ ከሎጂስቲክስ ጋር ታግለዋል፤ አሁንም ከሎጂስቲክስ ጋር እየታገሉ ነው”።
ሎይድ ኦስቲን የሩሲያ ኃይሎች “ከፍተኛ የመድፍ ጥይት እጥረት እያጋጠማቸው ነው” ብለዋል።
ኪየቭ የሞስኮን የማከማቻ ቦታዎችን በመምታቷ የሩሲያውያን የጥይት አቅም መውረዱን የመከላከያ ሚንስትሩ ተናግረዋል።
የሩሲያ ኃይሎች መሬት ላይ ከመንቀሳቀሳቸው በፊት ብዙ ቁጥር ያላቸውን ዙሮች በመተኮስ በመድፍ ላይ ይተማመናሉ ሲል ኦስቲን ተናግረዋል።
"ይህ አይነት አሰራር ብዙ ጥይቶችን ይጠይቃል። እናም ይንን ወደፊት ለመደገፍ እንደዚህ አይነት ጥይቶች እንዳላቸው እርግጠኛ አይደለሁም።” ብለዋል።
ኦስቲን በተጨማሪም ለዘጠኝ ወራት በተካሄደው ግጭት ውስጥ የሩሲያ እውነተኛ የመሣሪያዎች አቅርቦት "በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል" ብለዋል።
ሞስኮ እንደ ማይክሮ ቺፕስ ባሉ እቃዎች ላይ ባለው የንግድ እገዳ ምክንያት አቅርቦቱን በፍጥነት መተካት እንደማትችል መናገራቸውን ድፌንስ ፖስት ዘግቧል።