የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የዩክሬን የድርድር ቅድመ ሁኔታዎች “ከእውነታው የራቁ ናቸው” ሲሉ ተናገሩ
የዩክሬኑ መሪ ፤ፕሬዝዳንት ፑቲን በስልጣን ላይ እስካሉ ከሞስኮ ጋር የሰላም ድርድር አይኖርም ማለታቸው ይታወሳል
ላቭሮቭ "ምዕራቡ ዓለም ዘለንስኪን ለመቀጣት ፍላጎት እንዳለው ተጨባጭ ማስረጃዎችን ማየት እንፈልጋለን" ብለዋል
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የዩክሬን የድርድር ቅድመ ሁኔታዎች “ከእውነታው የራቁ ናቸው” ሲሉ ተናገሩ
ሩሲያን በመወከል በቡድን-20 ስብሰባ ላይ የሚገኙት ላቭሮቭ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት በሀገራቸው ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና ትክክል እንዳልሆነ ሞግተዋል፡፡
በሞስኮ እና ኪቭ መካከል እንደገና እንዲደረግ የሚፈለገውን ሰላም ንግግር እየተደናቀፈ ያለው በዩክሬን መሆኑ መናገራቸውም ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ላቭሮቭ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "ሁሉም ችግር እየመጣ ያለው በዩክሬን በኩል ነው፤ እሱም ድርድርን በመቃወም እና ግልጽ ያልሆኑ ሁኔታዎችን በማስቀመጥ ነው" ብለዋል፡፡
ከፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እንዲሁም እና ከጀርመን መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልዝ ጋር ባደረጉት ውይይት ጋር ባደረጉት ውይይት ይህንን የሩስያን አቋም ማስረዳታቸውንም ጭምር አስታውቀዋል።
የሩስያ እና የዩክሬን ባለስልጣናት በግጭቱ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ በሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን አሸማጋይነት የተስተናገዱ ስብሰባዎችን ጨምሮ - ጦርነትን ለመግታት ያለሙ ብዙ ያልተሳኩ ድርድሮች አድርገዋል።
ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ቱርክ አማካኝነትም እህል ወደ ውጭ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት መፈረማቸውም ይታወሳል።
ነገር ግን የዩክሬኑ መሪ ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በስልጣን ላይ እስካሉ ድረስ ኪቭ ከሞስኮ ጋር የሰላም ድርድር ማድረግ አትችልም ማለታቸው ጉዳዩ አሳሳቢ አድርጎታል።
ከፍተኛ የሩሲያው ዲፕሎማት ላቭሮቭ እንደሚሉት ከሆነ ግን የዓለም መሪዎች ጥፋቱ ማን ጋር እንደሆኑ ይታወቃል የሚል ነው፡፡
"ሾልዝ እና ማክሮን ይህ ሂደት (የሰላም ንግግር) የዩክሬኑ መሪ ህግ በማውጣትም ጭምር እያደናቀፉት መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉ"ም ነው ያሉት ላቭሮቭ፡፡
የሰላም ንግግር (ድርድር) ጉዳይ ለሩሲያ መቅረብ ያለበት ጥያቄ አይደለም እናም "ምዕራቡ ዓለም ዘለንስኪን ለመቀጣት እና ይህ ሊቀጥል እንደማይችል ለማስረዳት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተጨባጭ ማስረጃዎችን ማየት እንፈልጋለን" ሲሉም ተደምጠዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርገይ ላቭሮቭ፡፡
aXA6IDE4LjIxNy4yMjguMzUg ejasoft island