ሩሲያ፤ የተመድ መቀመጫ ከአሜሪካ እንዲነሳ የሚቀርብ ሃሳብን እንደምትደግፍ አስታውቃለች
ሩሲያ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት ከአሜሪካ ተነስቶ ወደሌላ ሀገር እንዲዛወር ፍላጎት እንዳላት አስታወቀች፡፡
ሩሲያ፤ ተመድ መቀመጫውን ከኒውዮርክ እንዲቀይር የሚነሳ ሃሳብን እንደምትደግፍ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ሞስኮ፤ የተመድ መቀመጫ ኒውዮርክ መሆኑ ቀርቶ ሌላ ገለልተኛ ሀገር እንዲሆንም ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች፡፡
የሩሲያ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ቨርሺኒ አሜሪካ የተመድ መቀመጫነቷን በመጠቀም ስራ እያስተጓጎለች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ የተመድ ዋና መስሪያ ቤት በሀገሯ በመገኘቱ ምክንያት የሩሲያ ዲፕሎማቶችን የቪዛ ሂደት እያስተጓጎለች ነው ስትል ሩሲያ ከሳለች፡፡
ሞስኮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማሻሻያ እንዲያደርግ ፍላጎት እንዳላትም ጠቅሳለች፡፡
ሩሲያ፤ አሜሪካ የተመድ መቀመጫነቷን በመጠቀመ እየፈጠረች ያለውን እንቅፋት በተመለከተ ግልግል እንደሚያስፈልግም ጠቅሳለች
የተመድን ስራና ውጤታማነት አሜሪካ እያበላሸች እንደሆነም ነው ሞስኮ ያነሳችው፡፡
አሜሪካ 12 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ማባረሯም አንዱ ማሳያ እንደሆነ ሞስኮ ገልጻለች፡፡ ሩሲያ፤ ከዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ብዙ ጊዜ እንደተነጋገረች ያነሱት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፤ አሁንም ሞስኮ ከዋና ጸሐፊው ጋር መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
ሩሲያ ይህንን የምታደርገው ችግሩን ለመፍታት አስፈላጊ በመሆኑ ነው ብላለች፡፡
አሜሪካ ለጠባብ ፖለቲካ ብላ ለሩሲያ እና ለሌሎች ተወካዮች ቪዛ አለመስጠቷ አሳዛኝ እንደሆነም ሩሲያ እየገለጸች ነው፡፡