አሜሪካ በተመድ ሲሰሩ የነበሩትን 12 ሩሲያውያን ዲፕሎማቶች ከኒውዮርክ አባረረች
አሜሪካ ዲፕሎማቶቹን "ለሀገራዊ ደህንነቴ ጠንቅ የሆኑ የስለላ ስራዎችን ሲሰሩ ነበሩ" ስትል ከሳለች
ሩሲያ በበኩሏ አሜሪካ ለወሰደችው እርምጃ “ተገቢውን ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ እሰጣለው” ብላለች
አሜሪካ ኒውዮርክ መቀመጫው ባደረገው የተመድ ዋና መስሪያ ቤት ይሰሩ የነበሩትን 12 ሩሲያውያን ዲፕሎማቶች አባረረች፡፡
አሜሪካ በዲፕሎማቶቹ ላይ የወሰደቸው እርምጃ ከብሄራዊ ደህንነት ጋር በተያያዘ እንደሆነም ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአሜሪካ ሚስዮን እንዳስታወቀው ከሆነ የሩስያ ዲፕሎማቶቹ "ለሀገራዊ ደህንነታችን ጠንቅ የሆኑ የስለላ ስራዎችን ሲሰሩ የነበሩ የመረጃ ሰዎች" ናቸው ሲል ገልጿል።
እርምጃ ለበርካታ ወራት የተደረገውን ጥናት መሰረት በማድረግ የተወሰደ ነውም ብለዋል ሚስዮኑ፡፡
በተመድ የአሜሪካ ምክትል አምባሳደር ሪቻርድ ሚልስ "ከአሜሪካ እንዲወጡ የተጠየቁት ዲፕሎማቶች እንደ ዲፕሎማት ኃላፊነታቸውን እና ግዴታቸውን ባልተወጡ ተግባራት ላይ የተሰማሩ እንደነበሩ" ተናግሯል።
ውጡ የተባሉት የአዘጋጇ ሀገር ብሄራዊ ደህንነት ስጋት ላይ እንዳያስገቡ በሚል እንደሆነም ገልጿል ምክትል አምባሳደሩ፡፡
አምባሳደር ሪቻርድ ሚልስ እርምጃው የተወሰደው በተመድ ዋና መሥሪያ ቤት ስምምነትና አሰራር መሰረት እንደሆነም አስረድቷል፡፡
በተመድ የሩሲያ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዝያ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከሆነ ዲፕሎማቶቹ እስከ መጋቢት7/22 ድረስ አሜሪካን ለቀው እንዲወጡ መጠየቃቸውን አረጋግጧል፡፡
አሜሪካ በዲፕሎማቶቹ ላይ ለወሰደችው እርምጃ “ሩሲያ ተገቢውን ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ ትሰጣለች”ም ሲሉም አክሏል አምባሳደሩ፡፡
ኔቤንዝያ በዩክሬን ስላለው የሰብአዊ ሁኔታን በማስመልክት በተመድ የጽታው ምክር ቤት ስብሰባ መጀመሪያ ላይ በአሜሪካ በኩል የቀረበው ሃሳብ የምክር ቤቱ መቀመጫ ከሆነችው ሃገር የማይጠበቅና ነገሮችን ይበልጥ የሚያባብስ ነው ብለውታልeል፡
አሜሪካና አጋሮቿ በዩክሬን የተፈጠረውን ሰሞነኛ አጀንዳ በመንተራስ የሞስኮን ኢኮኖሚ ያዳክማሉ ያሏቸው የተለያዩ ምጣኔ ሃብታዊ ማዕቀቦች በማዝነብ ላይ መሆናቸው ይታወቃል፡፡