የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት የጦር መሳሪያ እጥረት እንዳጋጠማቸው ገልጸዋል
የሩሲያ ጦር የዩክሬኗ አዲቭካ ከተማን መቆጣጠሩ ተገለጸ።
የሩሲያ ጦር በዛሬው እለት እንዳስታወቀው የዩክሬን ጦር ለቆ መውጣጡን ተከትሎ አዲቭካ የተባለችውን ከተማ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን አስታውቋል።
ሩሲያ አዲቭካ ከተማን መቆጣጠሯ በፈረንጆቹ ግንቦት 2023 ባክሙትን ከተቆጣጠረች በኋላ ያስቆጠረችው ትልቁ ድል እንደሆነም ተነግሯል።
የሩሲያ መከላያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው 1000 ኪሎ ሜትር ከሚሸፍነው የጦር ግንባር ውስጥ 8.6 ኪሎ ሜትርሩ በሩሲያ እጅ እንደወደቀ እና የሩሲያ ጦር አሁንም ወደፊት እየገፋ እንደሆነ አስታውቋል።
ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን አዲቭካ ከተማ በሩሲያ እጅ መግባቱ ትልቅ ድል ነው ያሉ ሲሆን ገልጸው፤ ለጦራቸውም የደስታ መልእክት አስተላፈዋል።
የዩክሬን በበኩሏ ጦር አዛዥ ኦሌክሳንደር ሲርይስኪ በሩሲያ ጦር ከበባ ውስጥ ከመግባት ለመዳን የሀገሪቱን ጦር ከአዲቭካ እንዲለቅ ማድረጉን አስታውቀዋል።
በምስራቃዊቷ የዩክሬን ከተማ ላለፉት አራት ወራት በተካሄደ ጦርነት ዩክሬን ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዷ የተነገረ ሲሆን፥ ሞስኮ በጦር መሳሪያም ሆነ በወታደሮች ብዛት ብልጫውን መያዟም ተመላክቷል።
በሩሲያ ወደተያዘችው ዶኔስክ መግቢያ በር የሆነችው አቭዲቭካ ለወራት በተካሄደው ጦርነት ፈራርሳለች፤ ከ34 ሺህ በላይ ሰዎች መኖሪያ በነበረችው ከተማ አሁን 1 ሺህ ገደማ ሰዎች ይኖሩባታል ተብሏል።