የሩሲያ ጦር ብዛት 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን እንደነበር ተገልጿል
ሩሲያ የጦሯ ብዛት ከ2 ሚሊዮን በላይ እንዲሆን ወሰነች፡፡
የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የብሄራዊ ጦር ብዛት ከ2 ሚሊዮን በላይ እንዲሆን መወሰናቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ ሩሲያ አሁን ላይ አንድ ነጥብ 9 ሚሊዮን ጦር ያላት ሲሆን አሁን ላይ የተለያዩ ስጋቶችን ታሳቢ በማድረግ የ137 ሺህ የጦር አባላትን እንዲጨምር ተወስኗል፡፡
የሩሲያ ጦር አባላት እንዲጨምር የተወሰነውን ውሳኔ ፕሬዝዳንት ፑቲን በፊርማቸው ማጽደቃቸውን ዘገባው ጠቁሟል፡፡
የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶ ከሁለት ወራት በፊት በስፔን መዲና ማድሪድ ባደረገው ጉባኤ ሩሲያ ዋነኛ የአውሮፓ ስጋት መሆኗን መወሰኑ ይታወሳል፡፡
የቃል ኪዳን ጥምር ጦሩ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የኔቶ አባል እሆናለሁ ማለቷን ተከትሎ በሩሲያ ጦር መደብደቧን ተከትሎ ነው፡፡
ሩሲያ በበኩሏ ኔቶ ሞስኮን በስጋትነት መፈረጁ ስህተት መሆኑን ጠቅሳ ጉዳዩ አሜሪካ ሩሲያን ከአውሮፓ ለመነጠል የጠነሰሰችው ሴራ ነው ማለቷ ይታወሳል፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 183ኛው ቀን ላይ የደረሰ ሲሆን ከ10 ሚሊዮን በላይ ዩክሬናዊያን ሀገራቸውን ጥለው መሰደዳቸውን ተመድ ገልጿል፡፡
እንዲሁም ከዘጠኝ ሺህ በላይ የዩክሬን ወታደሮች መገደላቸውን እና 20 በመቶ የዩክሬን ግዛትም በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስራ መውደቁን የኬቭ ባለስልጣናት ከቀናት በፊት መናገራቸው አይዘነጋም፡፡
ዩክሬን ከሩሲያ ጦር እየደረሰባተር ያለውን ወታደራዊ ጥቃት ለመመከት አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት የጦር መሳሪያዎችን በመለገስ ላይ ናቸው፡፡
ሩሲያ የጦሯ ብዛት ከ2 ሚሊዮን በላይ እንዲሆን ወሰነች
ፕሬዚዳንት ፑቲን አዲሱን አዋጅ በፊርማቸው አጽድቀዋል