ቀደም ሲል ጥራጥሬን የተመለከቱ ውይይቶች ተደርገው ነበር
ሩሲያ፣ቱርክና ዩክሬን ጥራጥሬን የተመለከተ ሌላ ውይይቶችን ሊያደርጉ መሆኑን አንካራ አስታወቀች፡፡
ቀደም ሲል ጥራጥሬ የሚተላለፍበትን ኮሪደር የተመለከተ ውይይት ቢደረግም አሁንም ተጨማሪ ንግግር ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል ተብሏል፡፡
ከዚህ በፊት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቱርኩ አቻቸው ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶሃን የጥራጥሬ መተላለፊያን በሚመለከት መነጋገራቸውን የሩሲያ ዜና አገልግሎት ታስ ዘግቦ ነበር፡፡
የቱርክ መከላከያ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው ሶስቱ ሀገራት የጥራጥሬ ምርት ወደ ዓለም ገበያ እንደት ይድረስ በሚለው ላይ ሌሎች ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮችን ያደርጋሉ፡፡
ቀደም ሲል ቭላድሚር ፑቲን እና ረሲፕ ጣኢብ ኤርዶሃን በጥራጥሬ ዙሪያ በስልክ ንግግር አድርገው ነበር፡፡
ምንም እንኳን የሀገራቱ መሪችዎች መነጋገራቸው ቢገለጽም ያስቀመጡት መፍትሄ ሆነ አቅጣጫ ስለመኖሩ የዜና ምንጮች አልጠቀሱም፡፡ ጥራጥሬን በሚመለከት ይደረጋሉ ተብለው በሚጠበቁ ቀጣይ ውይይቶች ላይ የተባበሩት መንግስታት እንደሚካተት ተገልጿል፡፡
ሩሲያ በተደጋጋሚ ጥራጥሬ ወደ ዓለም ገበያ እንዳይገባ እንቅፋት እንደሆነች ቢገለጽም ይህንኑ ስታስተባብል ቆይታለች፡፡
aXA6IDU0LjE5Ni4yNDguOTMg ejasoft island