ሩሲያ፤ የዩክሬን ጦር በግዙፉ “ዛፖሪዥያ ኒውክሌር ጣቢያ” ላይ ተኩስ ከፍቷል ስትል ከሰሰች
ሩሲያ፤ ዩክሬን የኒውክሌር ኃይል ጣቢያ ላይ የከፈተችው ተኩስ “ከባድ መዘዝ” የሚያስከትል ነው ስትል አስጠንቅቃለች
ዩክሬን በበኩሏ ክሬምሊንን በዛፖሪዥያ አቶሚክ ሃይል ማመንጫ ላይ “የኒውክሌር ሽብር” ፈጽማለች ስትል ከሳለች
የሩሲያ ቤተ መንግስት ክሬምሊን፤ የዩክሬን ጦር በግዙፉ የዛፖሪዥያ አቶሚክ ሃይል ማመንጫ ላይ ተኩስ ከፍቷል ስትል ከሰሰ።
በደቡብ ምስራቅ ዩክሬን የሚገኘው ዛፖሪዥያ አቶሚክ ሃይል ማመንጫ በአውሮፓ ትልቁና በዓለም ላይ ካሉት 10 ትላልቅ የኒውክሌር ኃይል ጣቢያዎች መካከል አንዱ ነው።
እናም ሩሲያ ፤ የዩክሬን ጦር ግዙፉን የኒውክሌር ጣቢያ ለማውደም ተኩስ ከፍተዋል በማለት ኪቭን ከሳለች።
ሩሲያ፤ ዩክሬን ግዙፉን አቶሚክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያ ማውደሟ “አሰቃቂ መዘዝ” ይዞ ሊመጣ እንደሚችል ልታውቅ ይገባል ስትል አስጠንቅቃለች።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "የዩክሬን ታጣቂ ሃይሎች የኒውክሌር ጣቢያን ማውደም ከዩክሬን ባለፈ ለአውሮፓ ምድር እጅግ አደገኛ ሊሆን የሚችል ተግባር ነው”ሲሉ ተደምጠዋል።
የዩክሬን አጋሮች "እንዲህ ዓይነቱ የዩክሬን እርምጃ እንዳይቀጥል ተጽእኖ ያድርጉ" ሲሉም ጠይቀዋል ቃል አቀባዩ።
ሩሲያ ይህን ትበል እንጅ ዩክሬን በተቃራኒው፤ የሩሲያ ኃይሎች በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ኩባንያው ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል የሚል ክስ በማቅረብ ላይ ናት።
ጥቃቱን ተከትሎ መግለጫ የሰጡት የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ "የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠንካራ ምላሽ" እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርበዋል።
ፕሬዝዳንቱ፤ በሞስኮ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች ለመጣል በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሼል ጋር መነጋገራቸውንም አስታውቋል ።
ክሬምሊንን “የኒውክሌር ሽብር” ፈጽማለች ሲሉም ከሷል ፕሬዝዳንት ዘሌንስኪ።