ዩክሬን የሩሲያ ኦርቶዶክስ ፓትሪያርክን በወንጀል ተፈላጊ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አካተተች
ፓትሪያርክ ክሪል ሩሲያ ዩክሬን ላይ የከፈተችውን ወረራ ደግፈዋል ብላለች ኪቭ
የዩክሬን የሀገር ውስጥ ሚኒስተር ፓትሪያርኩን ትናንት በተፈላጊ ዝርዝር አካቷል
ዩክሬን የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ክሪልን በተፈላጊ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አካተተች።
የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በትናትናው ዕለት ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን እና የ21 ወራት እድሜ ያለውን ጦርነት ይደግሉ በሚል ነው ፓትሪያርክ ክሪል በተፈላጊ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ያካተተው።
ዩክሬን ፓትሪያሪኩን በወንጀል ተፈላጊ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ያካተተችው የሀገሪቱ የፀጥታ አካላት በጦርነቱ ተሳትፎ አላቸው ብለው ከከሰሱ በኋላ ነው።
የዩክሬን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚፈለጉት ዝርዝር ውስጥ የፓትሪያሪክ ኪሪል በስም ለቋል የተባለ ሲሆን፣ "ከቅድመ ችሎት ምርመራ የተደበቀ ግለሰብ" ሲል ገልጿል።
ፓትሪያሪክ ክሪል በሩሲያ ውስጥ እንደመኖራቸው የዩክሬን የተፈላጊነት ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው ምንም የእስር ስጋት እንደማይፈጥር ተነግሯል።
የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ኪሪል ዩክሬን ከዚህ ቀደም ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ባላት ቤተክርስቲያን ላይ የምትፈጥረውን ተጽእኖ እንድታቆም ማሳሰባቸው ይታወሳል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ እያካሄደቸው ያለውን ወታደራዊ ዘመቻ ይደግፋሉ በሚል የሚወቀሱት ፓትሪያርክ ኪሪል ይህን ይበሉ እንጅ፤ የዩክሬን ቤተክርስቲያን የተለየ አቋም እንዳላት ስታሳውቅ ቆይታለች።
ቤተክርስቲያኗ ከሞስኮ ፓትርያርክ ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋርጫለሁ ማለቷም አይዘነጋም።