የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በ1 ሺህ 12ኛ ቀኑ ምን አዳዲስ ክስተቶችን አስተናግዷል?
ሩሲያ በዩክሬን መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃት ፈጽማ የሰዎች ህይወት አልፏል
በ24 ሰዓታት ውስጥ 55 የዩክሬን ድሮኖችን መትቶ መጣሉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል
ከተጀመረ 1 ሺህ 12ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የሩሲያ ክሬን ጦርነት ካሳለፈነው ሳምንት ወዲህ ወደ ከፍተኛ ግጭት መሸጋሩ እየተነገረ ይገኛል።
በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት አሁንም በምድር እና በአየር ላይ ውጊያ የቀጠለ ሲሆን፤ ሁለቱም ሀገራት ከሚሳዔል በተጨማሪ በድሮን የሚፈጽሙት ጥቃትም ተባብሶ ቀጥሏል።
የሩሲያ ጦር በምእራብ ዩክሬን በምትገኘው ቴርኖፒል በፈጸመው የድሮን ጥቃት አንድ ሰው መሞቱን እና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን የከተማዋ ወታራዊ አስተዳደር ቪያቸስላቭ ነጎዳ ተናግርዋል።
በደቡባዊ ዩክሬን ኬርሶን ከተማ ሩሲያ በድሮን በፈጸመቸው ጥቃትም ሶስት ሰዎች መሞታውን እና ሰባት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የክልሉ አስተዳዳሪ ኦሌክሳንደር ፕሮኩዲን ተናግረዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ማዕከላዊ ዲኒፕሮፔትሮቭስክ ክልል በሚሳዔል በፈጸመችው ጥቃት አራት ሰዎች መሞታቸውን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ የተናሩ ሲሆን፤ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውንም አስታውቀዋል።
ዩክሬን በሩሲያዋ ምእራብ ብሪያንስክ ክልል በድሮን በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ህጻን ልጅ ህይወት ማለፉን የክልሉ አስተዳዳሪ አሌክሳንደር ቦጎማዝ ተናግረዋል።
የሩሲያ የአየር መከላከያ ትናንት ሌሊት ወደተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች የተተኮሱ ድሮኖችን አየር ላይ መትቶ መጣሉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ሚኒስቴሩ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከዩክሬን የተተኮሱ ከ55 በላይ ድሮኖችን አየር ላይ መትቶ መጣሉንም አስታውቋል።
በምድር ላይ እየተደረገ ባለው ውጊያም የሩሲያ ጦር ወደፊት የሚያደርገውን ግስጋሴ እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ወታሮቹ በዩከሬኗ ዶኔስክ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኢሊንካ እና ፔትሪቭካ የተባሉ ሁለት መንደሮችን መያዙን አስታውቋል።
የዩክሬን ወታራዊ ምንጮች እንደተናገሩት ከሆነ በዩሬኗ ዶኔስክ ክልል ኩራኮቭ አካባቢ የሚገኘው የሩሲያ ጦር በቀን ከ200 እስከ 300 ሜትር ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን ተናረዋል።
ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገጠመችው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ፈጣን የተባለውን ግስጋሴ እያደረገች ዩክሬን ግዛቶች እየተቆጣጠረች መሆኑን የዘርፉ ተንታኞች ይናገራሉ።
የሩሲያ ጦር ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ 235 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት ተቆጣጥሯል የተባለ ሲሆን፤ ይህም የፈረንጆቹ 2024 አዲስ ክብረወሰን ነው።
ሩሲያ እየተገባደደ ባለው የፈረንጆቹ ህዳር ወር ብቻ 600 ካሬ ኪ.ሜ የዩክሬንን መሬት መቆጣጠሯንም ዲፕ ስቴት የተባለውን እና ለዩክሬን ጦር ቅርበት ያለውን ተቋም ዋቢ በማድረግም የወጣ መረጃ ያመለክታል።