የሩሲያ እርምጃ ያየለበት የዩክሬን-ሩሲያ ጦርንት ምን አዳዲስ ነገሮችን እያስተናገደ ነው?
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት 814 ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ሩሲያ አዳዲስ ስፍራዎችን እየተቆጣጠረች ነው
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከ120 እስከ 130 የሚደርስ F-16 እና ሌሎችም ዘመናዊ ጦር ጄቶች ያስፈልጉናል ብለዋል
የሩሲያ ዩክሬን ጦርንት ከተጀመረ ዛሬ 814ኛ ቀኑን ያስቆጠረ ሲሆን፤ ሩሲያ በአንድ አንድ ስፍራዎች የበላይነትን እየተቀዳጀች እንደሆነ ተነግሯል።
ሩሲያ ካሳለፍነው ሳምንት አርብ ጀምሮ በዩክሬን የምትፈጽምን ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ ማጠናከሯን ተከትሎ ጦሯ ባለፉት ቀናት ውስጥ ቢያስ 9 መንደሮችን እና አነስተኛ ከተሞችን መያዝ ችሏል።
ሩሲያ ወታደሮቿ ዩክሬኗ ሁለተኛ ግዙፍ ከተማ ካርኪቭን በሰሜን ምስራቅ በኩል የምታዋስነውን ቮቭቻንስክ የተባለች ከተማ መቆጣጠራቸውን ማስታወቋም ይታወሳል።
የሩሲያ ጦር ካርኪቭ የተሰኘችውን የዩክሬን ሁለተኛዋ ትልቋ ከተማን ለመቆጣጠር ዓላማ አድርጎ እየገሰገሰ ሲሆን፤ ዩክሬን በበኩሏ ካርኪቭ ከተማን ለሩሲያ ማስረከብ የማይታሰብ ነው ብላለች።
የዩክሬን ሩሲያ ጦርንት ምን አዳዲስ ነገሮችን እያስተናገደ ነው?
ሩሲያ ትናንት ምሽት በካርኪቭ ከተማ ባደረሰችው የአየር ድብደባ 2 ሰዎች ሲሞቱ 19 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን የካርኪቭ አስተዳዳሪ ኦሌህ ሳይኔሁቦቭ በቴሌግራም ገጻቸው አስታውቀዋል።
ዩክሬን በደቡባዊ ሩሲያ ቤልግሮድ ክልል በድሮን በፈጸመችው ጥቃት 1 ሰዎ ሲሞት አንድ ሰው ደግሞ ሰሙሰሉን የክልሉ አስተዳዳሪ ቫይቼልሳቭ ግላድኮቭ ተናግረዋል።
800 ሺህ የሚሆኑ ሲቪል ዜጎች ከየክሬኗ ቮቭቻንስክ አነስተኛ ከተማ ለቀው አንዲወጡ መደረጋቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፤ ሩሲያ በደቡብ ምስራቅ በኩል የምታደረገውን ውጊያ አጠናከራ እንደመትቀጥል ይጠበቃል ያሉ ሲሆን፤ ዩክሬን ያላት የአየር መከላከያ ስርዓት 25 በመቶ ብቻ ነው ሲሉም አሳስበዋል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ የሩሲያ ጦር በሰሜን ምስራቅ ድንበር በኩል እስከ 10 ኪሎ ሜትር ድረስ ወደ ዩክሬን ዘልቀው በመግባት መያዙን አስታውቀው፤ አሁን ላይ ዩክሬን ጦር እንቅስቃሴያቸውን መግታቱን ገልጸዋል።
ዘለንስኪ አክለውም አሁን ላይ በካርኪቭ ከተማ ያለው ሁኔታ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጸው፤ ነገር ግን አሁንም የተረጋጋ ሁኔታ የለም ብለዋል።
ዩክሬን ከሩሲያ ጋር የአየር ላይ ውጊያ ለማድረግ ከ120 እስከ 130 የሚደርስ F-16 እና ሌሎችም ዘመናዊ ጦር ጄቶች እንደሚያስፈልጋት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ አስታውቀዋል።
ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ እስረኞች ወደ ዩክሬን ጦር ተቀላቅለው የሚዋጉበት አዲስ ህግም ትናነት የፈረሙ ሲሆን፤ ዛሬ ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል።