ወደ አዲስ የግጭት ምዕራፍ በተሸጋገረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ምን አዳዲስ ክስተቶች እያስተናገደ ነው?
የሩሲያ ጦር አዲስ መንደር የተቆጠጠር ሲሆን፤ በቀን እስከ 300 ሜትር ድረስ ወደፊት እየተገሰገሰ ነው ተብሏል
ዩክሬን ከሩሲያ ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች ለተደቀነባት አዲስ ስጋት አጋሮቿን ዘመናዊ የአየር መከላከያዎችን ጠይቃለች
ዩየሩሲያ ክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ያሳለፈነው ሳምንት የነበረው ክስተት ግጭቱ ወደ ከፍተኛ ሁኔታ መሸጋሩ የታየበት ነበር።
ጦርነቱ እንደ አዲስ ያገረሸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን የአሜሪካ የረጅም ርቀት ሚሳዔሎችን ተጠቅማ የሩሲያ ግዛት ውስጥ ጥቃት እንደትፈጽም መፍቀዳቸውን ተከትሎ ነበር።
ሞስኮ ዩክሬንን በአዲስ የመካከለኛ ርቀት ባሊስቲክ መሳሪያ ስትመታ የአለም አቀፉን ማህበረሰብ አስደንግጦ ተጨማሪ ስጋትን ከፍ በማድረግ የሩሲያ ዩክሬን የሚዔል ፍጥጫውን ትንሽ ረገብ አድርጎታል።
ነገር ግን በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል በዩክሬን ውስጥ በምድር ላይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት አሁንም የቀጠለ ሲሆን፤ የሩሲያ ጦር ወደፊት የሚያደርገውን ግስጋሴ እንደቀጠለ ነው ተብሏል።
የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን ዶኔስክ ክልል ውስጥ የምትገኝ ኖቮድማይትሪክቫ የተባለች መንደር መቆጣጠሩን እና አዳዲስ ስፍራዎችን መያዙን አጠናክሮ መቀጠሉን የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የዩክሬን ጦር ወታደራዊ አዛዥ የሩሲያ ጦር ተቆጣጠርኩት ያለው ስፍራ የሩስያ ሀይሎች በጦርነት ከተሳተፉባቸው ስምንት መንደሮች መካከል አንዱ ነው ብለዋል።
የዩክሬን ወታራዊ ምንጮች እንደተናገሩት ከሆነ በዩሬኗ ዶኔስክ ክልል ኩራኮቭ አካባቢ የሚገኘው የሩሲያ ጦር በቀን ከ200 እስከ 300 ሜትር ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን ተናረዋል።
በአካባቢው ያለው ሁኔታ የበለጠ "የከፋ" እንደሆነ የገለጸው ምንጩ፤ ለሩሲያ ግን ወሳኝ እና ትልቅ ሽልማት ነው በማለት ገልጿል።
የዩክሬን ባለስልጣናት እንደተናገሩት ከሆነ በትናትናው እለት ሩሲያ በሰሚይ ክልል በፈጸመችው የድሮን ጥቃት 2 ሰዎች ሲሞቱ፤ 12 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
ከጦርነቱ በተጨማሪ ወታራዊ እና የከባድ የጦር መሳሪያ ፍጥጫው አሁንም እያገረሸ ሲሆን፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አዲሱን “የኦሬሽኒክ” ባለስቲክ ሚሳኤል በጅምላ እንዲመረት ትዕዛዝ መስጠታቸው ተነግሯል።
“የኦሬሽኒክ” ባለስቲክ ሚሳኤል ፍጥነት ከድምጽ ፍጥነት 10 እጥፍ ፍጥነት እንደሚጓዝና በ5 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ የሚገኝ ኢላማን መምታት እንደሚችል ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ከሩሲያ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል እንደተተኮሳባት የተናገረችው ዩክሬን አለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህን መሳርያ ጥቅም ላይ እንዳይውል ጫና እንዲያሳደሩ በመጠየቅ ላይ ትገኛለች።
ዩክሬን ከሩሲያ ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች ለተደቀነባት አዲስ ስጋት ምላሽ ለመስጠት አጋሮቿ ዘመናዊ የአየር መከላከያ ዘዴዎችን እንዲሰጧ እንደምትፈልግ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ተናግረዋል።