ሩሲያና አሜሪካ ወደ ቀጥታ ጦርነት ለመግባት ከጫፍ ደርሰዋል ተባለ
ሩሲያ ፑቲንን ለመግደል አልሟል ካለችው የክሬምሊን ቤተ መንግስት ጥቃት ጀርባ አሜሪካ አለች ስትል ከሳለች
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር፤ “ከአሜሪካ ጋር የጦርነት አፋፍ ላይ ነን” ብለዋል
ሩሲያና አሜሪካ ወደ ቀጥታ ጦርነት ለመግባት ከጫፍ መድረሳቸውን በሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ሰርጌይ ራይባኮቭ አስታወቁ።›
ባሳለፍነው ሳምንት በሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን መኖሪያ በሆነው የክሬምሊን ቤተ መንግስት ላይ የድሮን ጥቃት ለመፈጸም ሙከራ መደረጉ ተገልጿል።
ፑቲንን ለመግደል አልሟል ከተባለው ጥቃት ጀርባ አለች ሲል የሩሲያው ክሬምሊን ቤት መንግስት ከሷል።
ይህንን ተከትሎም አሜሪካ እና ሩሲያ ቃታ ስበው እርስ በእርሳቸው ለመታኮስ ከጫፍ መድረሳቸውን ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ሰርጌይ ራይባኮቭ የተናገሩት።
- ሩሲያ፤ አሜሪካና ዩክሬን በክሬምሊን ላይ የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት ውድቅ ማድረጋቸው "አስቂኝ ነው" አለች
- በፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የግድያ ሙከራ ተፈጸመ
“አሁን ላይ ከአሜሪካ ጋር ወደ ቀጥታ ጦርነት ለመግበጣ ጫፍ ላይ ነን” ያሉት ሚኒስትር ደኤታው፤ “ከአሜሪካ ጋር ያለን ግንኙነት ወደ ወታደራዊ ግጭት እንዳይገባ የሚቻለንን ሁሉ እየሰራ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
ሰርጌይ ራይባኮቭ አክለውም በሁለቱ ሀገራት መካከል አሁን ላይ ትክክለኛ ዲፕሎማሲ የለም ያሉ ሲሆን፤ ምክንያቱ ደግሞ አሜሪካ ጦርነቱን የማባባስ ስራ ላይ ስለተጠመደች ነው ሲሉም አስታውቀዋል።
አሜሪካ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገች ባለው ጦርነት ላይ በቀጥታ እየተሳተፈች ነው ያሉ ሲሆን፤ በሀገራን ላይ ሁሉን አቀፍ ጦርነት ለመቀስቀስ እየሰራች ነው ሲሉም ከሰዋል።
በክሬምሊን ቤተ መንግስት ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ሩሲያ፥ ዩክሬ በቀጥታ ጥቃቱን እንደፈጸመች እንዲሁም አሜሪካ ደግሞ ከጥቃቱ ጀርባ አለች ስትል መክሰሷ ይታወሳል።
ዩክሬንም ይሁን አሜሪካ በክሬምሊን ቤተ መንግስት ጥቃት ላይ እጃቸው አለበት መባሉን ባወጡት ግለጫ ውድቅ አድርገዋል።
ይህንን ተከትሎ ክሬምሊን ቤት መንግስት ባወጣው መግለጫ፤ አሜሪካና ዩክሬን በክሬምሊን ላይ የተፈጸመውን የድሮን ጥቃት ውድቅ ማድረጋቸው "አስቂኝ ነው" ብሏል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩሉ፤ በክሬምሊን ቤተ መንግስት ጥቃት ላይ የተሳተፉ በሙሉ እንደሚለቀሙ እና ከባድ የቅጣት እንደሚቀበሉ እርግጠኛ ነኝ ሲል መዛቱም ይታወሳል።