በምዕራባውያን ሀገራት ለዩክሬን ኑክሌር ስለማስታጠቅ የሚደረጉ ውይይቶች ኃላፊት የጎደላቸው ናቸው- ሩሲያ
ፔስኮ ምዕራባውያን ፑቲንን በጥንቃቄ ሊያዳምጧቸው ይገባል ብለዋል
ቀደም ሲል የሩሲያ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑት ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ ምዕራባውያን ለዩክሬን የኑክሌር የጦር መሳሪያ የሚያስታጥቁ ከሆነ ሞስኮ በኑክሌር የአጸፋ ምላሽ ልትሰጥ ትችላለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል
በምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ስለማስታጠቅ የሚደረጉ ውይይቶች "ፍጹም ኃላፊነት የጎደላቸው ናቸው"ሲሉ የሩሲያ ቤተመንግስት ክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
የኒው ዮርክ ታይምስ ባለፈው ሳምንት በስም ያልጠቀሳቸው ምዕራባውያን ባለስልጣናት የአሜሪካ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ምንም እንኳን የከፋ ውጤት ሊያስከትል ቢችልም ለዩክሬን የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሊሰጡ ይችላሉ ማለታቸውን ዘግቧል።
ፔስኮ አስተያየቶቹን የሰጡት በስም ያልተጠቀሱ ግለሰቦች መሆናቸውን እና ይህም ኃላፊነት እንዳይሰማቸው አድርጓል። ምዕራባውያን ፑቲንን በጥንቃቄ ሊያዳምጣቸው ይገባል ብለዋል ፔስኮቭ።
ቀደም ሲል የሩሲያ ከፍተኛ የጸጥታ ባለስልጣናት የሆኑት ዲሜትሪ ሜድቬዴቭ ምዕራባውያን ለዩክሬን የኑክሌር የጦር መሳሪያ የሚያስታጥቁ ከሆነ ሞስኮ እንደተጠቃች ስለምትቆጥረው በኑክሌር የአጸፋ ምላሽ ልትሰጥ ትችላለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በቅርቡ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ዩክሬን የረጅም ርቀት ሚሳይሎችን ተጠቅማ ሩሲያ ግዛት ውስጥ ያሉ ኢላማዎችን እንድትመታ ከፈቀዱ በኋላ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከፍተኛ ጡዘት ላይ ደርሷል።
ይህን ተከትሎም ሩሲያ በጣም ፈጣን የተባለውን ኦርሼኒክ ሚሳይል ወደ ዩክሬን ዲኒፔሮ ግዛት አስወንጭፋለች።