በዩክሬን በደርዘን የሚቆጠሩ የሩሲያ ወታደሮች በመገደላቸው ቁጣ ተቀሰቀሰ
በምስራቅ ዩክሬን በሚገኝ አንድ የሙያ ኮሌጅ በተነሳ የእሳት አደጋ 63 የሩሲያ ወታደሮች ህይወታቸው አልፏል
የሩስያ መከላከያ ሚንስቴር ወታደሮቹ የሞቱት በየክሬን ጥቃት ነው ብሏል
በዩክሬን በደረሰ የእሳት አደጋ በደርዘን የሚቆጠሩ የሩስያ ወታደሮች መሞታቸውን ተከትሎ ንዴታቸው የጨመረ ሩስያዊያን “አደጋን ችላ” ያሉ አዛዦች እንዲቀጡ ጠይቀዋል።
በፈረንጆቹ አዲስ አመት ዋዜማ በምስራቅ ዩክሬን ውስጥ ሩሲያ በተቆጣጠረችው ማኪይቭካ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ የሙያ ኮሌጅ ውስጥ በእሳት አደጋ 63 ወታደሮች ህይወታቸው አልፏል።
የሩሲያ መከላከያ ሚንስቴር ደረሰ በተባለው ድንገተኛ ፍንዳታ 63 ወታደሮች መገደላቸውን እንግዳ በተባለው መግለጫ ገልጿል።
የሩስያ ተቺዎች ወታደሮቹ በስፍራው ከጥይት ክምር ጋር ተቀምጠው እንደነበር ተናግረዋል። የሩስያ መከላከያ ሚንስቴር ግን በአሜሪካ ሰራሽ ማስወንጨፊያ በተተኮሰ አራት የሮኬቶች ጥቃት ወታደሮቹ ሞተዋል ብሏል።
በአዲስ ዓመት ዋዜማ በማኪይቭካ ላይ የደረሰው “ጥቃት” ሩሲያ በኪየቭ እና በሌሎች የዩክሬን ከተሞች በምሽት የአውሮፕላን ጥቃቶችን እየፈጸመች ባነበረበት ወቅት ነው ተብሏል።
ዩክሬን በበኩሏ በማኪይቭካ የሞቱት ሩሲያውያን በመቶዎች የሚቆጠሩ ናቸው ያለች ሲሆን፤ በሩስያ የተሾሙ ባለስልጣናት ግን የተጋነነ ነው ብለውታል።
የሩስያ ወታደራዊ ጸሀፊዎች የጥፋቱ መጠን ከዩክሬን ሮኬቶች ክልል ውስጥ መሆኑን አዛዦች ቢያውቁም ጥይቶችን በአንድ ህንጻ ውስጥ የማጠራቀም ውጤት ነው ብለዋል ።
ሮይተርስ ዩክሬን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባለው ግዛት ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነቱን አልወሰደችም ብሏል። ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ በሰኞ ምሽት ንግግራቸው የማኪይቭካ ጥቃትን አላነሱም ተብሏል።
ነገር ግን የዩክሬን ጦር ኃይሎች ጽ/ቤት የማኪይቭካ ጥቃት "በሩሲያ የሰው ኃይል እና በወታደራዊ መሳሪያዎች ላይ የተፈጸመ ጥቃት" ብሏል። በሰው ህይወት ላይ የደረሰውን ጉዳት ግን ባይገልጹም 10 ወታደራዊ ቁሶች ወድመዋል ግን ብለዋል።