የሩሲያ ጦር ከቧት የነበረችውን የዩክሬኗን ማሪዎፖል ከተማ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
የሩሲያ መከላከያ አሁንም በማሪዎፖል የመሸጉ የዩክሬን ወታደሮች መኖራቸውን ገልጿል
የማሪዎፖል ከተማ ወደ ዶምባስ ግዛት ለመቀንቀሳቀስ የሚያችል ስትራቴጅካዊ ቦታ መሆኑን ሩሲያ ስትገልጽ ቆይታለች
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሩሲያ ጦር ከበባ ስር የነበረችውም የወደብ ከተማዋ ማሪዎፖል በሩሲያ ጦር ቁጥጥር ስር መዋሏን አስታወቀ፡፡
የሩሲያው አርቲ የሩሲያን መከላከያ ሚኒስቴር ሰርጌይ ሾጊን ጠቅሶ እንደዘገበው በማሪዎፖል በሚገኘው የአዞቭስታል ብረት ፋብሪካ ውስጥ ወደ 2ሺ የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮች መሽገው ይገኛሉ፡፡
የሩሲያ ጦር የማሪዎፖልን ከተማ ዶምባስ ግዛት ለመቀንቀሳቀስ የሚያችል ስትራቴጅካዊ ቦታ መሆኑን ሩሲያ ስትገልጽ ቆይታለች፡፡
ሩሲያ ጎረቤቷ ዩክሬን ኔቶን እቀላቀላለሁ ማለቷን ተከትሎ ከፈረንጆች የካቲት 24፤ 2022 ጀምሮ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄድ መጀመሯ ይታወቃል።
በየሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከ5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት ለመሰደድ እንደተገደዱ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ያወጣው ሪፖርት ያመለክታል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ እየወሰደች ያለውን ወታደራዊ እርምጃ ከጀምሩም ቢሆን የተቃወሙት ምዕራባውያን፤ ሩሲያን ያዳክማሉ ያሉዋቸው ማዕቀቦች ሲጥሉ እየተስተዋሉ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ባደረገው ስብሰባ ሩሲያ ዩክሬንን መዉረሯን የሚያወግዘዉን የዉሳኔ ሀሳብ በአብላጫ ድምጽ ማጸደቁም እንዲሁ የሚታወስ ነው።
የተመድ ጠቅላላ ጉባኤም ሩሲያ ተመድ የሰብአዊ መብት ምክርቤት በአብላጫ ድምጽ እንድትታገድ ያደረገ ሲሆን ሩሲያም ይህን ተከትሎ ከም/ቤቱ አባልነት መውጣቷን ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
ሩሲያ ከም/ቤቱ የታገደችው ሩሲያ ጦር በዩክሬን ባካሄደው ጦርነት፣በሰብአዊነት ላይ ወንጅል ፈጽሟል በሚል ነበር፡፡