ዩክሬን የማሪዎፖል ከተማን ለመከላከል “ወታደሮቼ እስከ መጨረሻው ይዋጋሉ” አለች
አሁናዊ የሩሲያ ሃይሎች ዋና ትኩረት በምስራቃዊ ዩክሬን ላይ የሚሰነዘረውን ወታደራዊ ጥቃት ላይ ነው ተብለዋል
ሩሲያ ማሪዎፖል ከተማን መቆጣጠር ከቻለች “ለሩሲያ ጦር ትልቅ ስትራቴጂካዊ ድል ይሆናል” ተብሏል
በሩሲያ ሃይሎች ከበባ ውስጥ የምትገኘውን የማሪዎፖል ከተማ ለመከላከል የዩክሬን ወታደሮች 'እስከ መጨረሻ ይወጋሉ' ሲሉ የዩክሬኑ ጠቅላይ ሚኒሰትር ደኒስ ሽማይሃል ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት፤ሩሲያ የዩክሬን ወታደሮች እጃቸው እንዲሰጡ ያቀረበችውን የጊዜ ገደብ ማብቃቱን ተከትሎ ነው፡፡
በሌላ በኩል ዩክሬን፡በምስራቃዊ ዩክሬን የምትገኘው የዶምባስ ግዛት ለሩሲያ አሳልፋ እንደማትሰጥ ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ አስታውቋል፡፡
ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሩሲያ ሃይሎች ዋና ትኩረት በምስራቃዊ ዩክሬን ላይ የሚሰነዘረውን ወታደራዊ ጥቃት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካው የዜና ወኪል ኤቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት ከሆነ፡ ሩሲያ በማርዩፖል ከተማ የሚገኙ የዩክሬን ወታደሮች እስከ እሁድ አመሻሽ አከባቢ እጃቸው እንዲሰጡ፡ ያስቀመጠቸው ቀነ ገደብ ውድቅ መደረጉ ገልጿል፡፡
ማርዩፖል ከተማ አሁንም በዩክሬን ሃይሎች ስር ናት የሚሉት ጠቅላይ ሚኒሰትሩ “የእኛ ወታደሮች አሁንም በቦታቸው ማርዎፖል ላይ ናቸው፡ አሁንም እስከመጨረሻ የሚፋለሙ ይሆናል”ም ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ደኒስ ሽማይሃል እንዲህ ቢሉም ግን የሩሲያ ጦር ከተማዋን በቁጥጥሩ ስር መሆኗ በመግለጽ ላይ ነው፡፡
ሩሲያ እንደምትለው ወታደሮቿ ከተማዋን መቆጣጠር ከቻሉና ሩሲያን በሚደግፉ ታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ወዳሉ የምስራቅ ዩክሬን ግዛቶች መዝለቅ ከቻሉ፤ ለሩሲያ ጦር ትልቅ ስትራቴጂካዊ ድል ይሆናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩክሬን በችግር ላይ የሚገኙትን ዜጎቿ እና የቆሰሉ ወታደሮቿን ከከተማዋ ለማስወጣት ፤ የሩሰያ ሃይሎች መውጫ መንገድ ክፍት እንዲያደርጉ ቢጠይቁም፤ በሩሲያ በኩል እስካሁን የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩ ተገልጿል፡፡
የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ድርጅቶች መረጃ እንሚያሳው ከሆነም ታዲያ፤ በማርዎዩፖል ከተማ የሚገኙ ዩክሬናውያን በከፍተኛ ችግር ውስጥ ናቸው፡፡
ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ በትናንትናው እለት ከሲኤንኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ጦርነቱ እንዲቆም የዶምባስ ግዛትን ጨምሮ የተወሰኑ የምስራቅ ዩክሬን አከባቢዎች ለሩሲያ መስጠት የሚለው ሃሳብ እንደማይቀበሉት ተናግሯል፡፡
‘‘በዚህ ጉዳይ ዩክሬናውያን ግልጽ አቋም አላቸው፡፡ እኛ የሌሎችን ግዛት ይሰጠን አላልንመ፡ በዛው ልክ የኛ የሆነውም አንሰጥም’’ም ነበር ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡