የሩሲያ ኃይሎች ሁለት የዩክሬን መንደሮችን መቆጣጠራቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ
ሩሲያ በ2022 ልዩ ያላቸውን ወታደራዊ ዘመቻ በዩክሬን ላይ ከከፈተች ወዲህ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የሩሲያ ወታደሮች በምስራቅ ዩክሬን ፈጣን ግስጋሴ እያደረጉ ይገኛሉ
የሩሲያ ኃይሎች ሁለት የዩክሬን መንደሮችን መቆጣጠራቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሩሲያ ኃይሎች በሰሜን ምስራቅ ዩክሬን ካርኪቭ እና በምስራቃዊ ዶኔስክ ግዛት ሁለት መንደሮችን መቆጣጠራቸውን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በትናንትናው እለት አስታውቋል።
የዶኔስክ ግዛት ሩሲያ ሁለት ከተሞችን ለመያዝ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኃይል ያከማቸችበት ግዛት ነው።
በዶኔስክ ግዛት ወደፊት እየገፉ ያሉት የሩሲያ ኃይሎች ወሳኝ የሎጂስክ ማስተላለፊያ የሆነችውን እና የድንጋይ ከሰል ማዕድን ማውጫ የሚገኝባትን የፖክሮቭስክ እና በደቡብ በኩል ኩራሆቭ ከተሞችን ለመያዝ ወደፊት እየገፉ ነው።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር መግለጫ እንዳስታወቀው በሰሜን ዶኔስክ ግዛት ውስጥ በምትገኘው የኩፒያንስክ ከተማ አቅራቢያ የምትገኘውን የሎዞቫ መንደር ተቆጣጥረዋል። ከኩሳኮቭ ከተማ በስተሰሜን በከል የምትገኘውን የሶንትስቭካ መንደርም ተይዛለች።
ሚኒስቴሩ ባለፈው ቅዳሜ በኩራኮቭ ከተማ አቅራቢያ የምትገኘውን ኮስቲያንቲኖፖልስክ መንደርን መቆጣጠር ችለዋል።
የዩክሬን ጦር እነዚህ መንደሮች በሩሲያ እጅ ገብተዋል ስለሚባለው ሪፖርት ያሉት ነገር የለም።
ነገርግን ጦሩ በሁለቱ መንደሮች ዙሪያ የሩሲያ ኃይሎች ከባድ ጥቃት ከፍተው እንደነበር ገልጿል።
ሩሲያ በ2022 ልዩ ያላቸውን ወታደራዊ ዘመቻ በዩክሬን ላይ ከከፈተች ወዲህ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የሩሲያ ወታደሮች በምስራቅ ዩክሬን ፈጣን ግስጋሴ እያደረጉ ይገኛሉ።