
የበረራ ሰራተኞቹ ኦችጋቫ በበረራ ወቅት ባዶ በነበረ ቦታ ተቀምጦ እንደነበር ለመርማሪዎች ተናግረዋል
ፖስፖርት እና ቲኬት ሳይዝ አሜሪካ የገባው ግለሰብ ተከሰሰ።
ፖስፖርት እና ቲኬት ሳይዝ ወደ አሜሪካ፣ ሎስአንጀለስ የገባው ሩሲያዊ ግለሰብ በወንጀል ተከሷል።
ይህ ግለሰብ ለኤፍቢአይ እንደተናገረው ያለፖስፖርት እና ያለቲኬት ከዴንማርክ ወደ ሎስአንጀለስ የተደረገውን የበረራ ፍተሻ እንዴት እንዳለፈ አያውቅም።
ሰርጌ ቭላድሚሮቪች ኦችጋቫ ከኮፐንሀገን በተነሳው የበረራ ቁጥሩ 931 በሆነው የስካንዲኒቪያን አየርላየንስ ተሳፍሮ ህዳር አራት ነበር ሎስአንጀለስ ያረፈው።
የአሜሪካ የከስተም እና ቦርደር ፕሮቴክሽን ባለሙያ እንደገለጹት የኦችጋቫ ስም በአለምአቀፍ በረራ ዝርዝር ውስጥ አለመካተቱን በሎስአንደለስ ለሚገኘው የፌደራል ፍርድ ቤት አስረድተዋል።
አጭበርብሮ በመጓዝ የተከሰሰው ግለሰቡ ጥፋተኛ አይደለሁም ብሏል።
ከማክሰኞ ጀምሮ በቁጥጥር ስር የዋለው የኦችጋ ተከላካይ ጠበቃ በጉዳይ ላይ መረጃ እንዳልሰጠው ኤፒ ዘግቧል።
የበረራ ሰራተኞቹ ኦችጋቫ በበረራ ወቅት ባዶ በነበረ ቦታ ተቀምጦ እንደነበር ለመርማሪዎች ተናግረዋል።
በበረራ ወቅት ኦችጋቫ ከቦታ ቦታ ሲቀይር እንደነበር ተገልጿል።