ምዕራባውያን፤ ሞስኮ በኪቭ ላይ በፈጸመችው ወረራ በቡድን 20 ጉባዔ ላይ የመቀመጥ ሞራል የላትም እያሉ ነው
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በኢንዶኔዥያ በሚካሄደው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ አይገኙም ተባለ።
በየካቲት ወር ሩሲያና ዩክሬንን ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና ፑቲን በአንድ ስብሰባ ላይ ሲገኙ ይህ ጉባኤ የመጀመሪያው ይሆን ነበር።
የፑቲን በጉባኤው አለመታደም ከዩክሬን ጋር በገቡት ጦርነት ከዩናይትድ ስቴትስ እና ከአጋሮቿ ጋር ሊፈጠር የሚችለውን ፍጥጫ አስወግዷል ተብሏል።
የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሚቀጥለው ሳምንት በኢንዶኔዥያ በሚካሄደው የቡድን 20 ጉባኤ ላይ እንደማይገኙ የኢንዶኔዢያ መንግስት ባለስልጣን ተናግረዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፣የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ እና ሌሎች የዓለም መሪዎች በፈረንጆቹ ህዳር 15 ቀን በባሊ ኢንዶኔዢያ በሚጀምረው የሁለት ቀናት ስብሰባ ይሳተፋሉ።
ጉባዔው ባይደን እና ፑቲን ጦርነቱ ከተነሳ በኋላ ቢገናኙ የመጀመሪያ ጊዜ ይሆን እንደነበር እንደነበር ኤቢሲ ኒውስ አሶሼትድ ፕረስን ጠቅሶ ዘግቧል።።
የቡድን 20 ዝግጅቶች ድጋፍ ዋና ዳይሬክተር ሉሁት ቢንሳር ፓንጃይታን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የሩስያን ልዑካን ይመራሉ።
"የኢንዶኔዥያ መንግስት የሩሲያ መንግስት ውሳኔን ያከብራል። ፕሬዝዳንት ፑቲን ራሳቸው ከዚህ ቀደም ለፕሬዚዳንት ጆኮ ዊዶዶ በጣም ወዳጃዊ በሆነ የስልክ ውይይት አብራርተውታል" ብለዋል።
ብሪታኒያን ጨምሮ በርካታ የምዕራባውያን ሀገራትም እንዲሁ ሞስኮ በኪቭ ላይ በፈጸመችው ወረራ በቡድን-20 ጉባዔ ላይ የመቀመጥ “የሞራል መብት” የላትም ማለታቸው ይታወሳል።
የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሊድሚር ዘለንስኪ “ፐሬዝዳንት ፑቲን በቡድን 20 ጉባዔ የሚገኝ ከሆነ ላይ አልሳተፍም” ማለታቸውም አይዘነጋም።