የቤተክርስቲያኗ ፍርድ ቤት እንደገለጸው ኡምንስኪይ ፖትሪያርክ ክሪል ተግባራዊ እንዲሆን ያዘዙትን ጸሎት ለማድረስ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፣ የገቡትን ቃል ጥሰዋል
ሩሲያ ዩክሬንን ድል እንድታደርግ ጸሎት አላደርስም ያሉ ቄስ የመባረረ እጣፈንታ አጋጥሟቸዋል።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ድል እንድትቀዳጅ ፈጣሪ እንዲመራት የሚጠይቀውን ጸሎት አላደርስም ያሉ ታዊቂ ቄስ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊባረሩ ነው ተብሏል።
የቤተክርስቲያኗ ፍርድ ቤት ቅዳሜ እለት ባተመው ውሳኔ የቅስና መሀላቸውን ጥሰዋል ያላቸው ቄስ አሌክሲይ ኡምኒስኪይ ከቤተክርስቲያኗ አገልግሎት መውጣት አለባቸው ሲል ወስኗል።
ውሳኔው እንዲጸድቅ ለሩሲያው ፖትሪያርክ ፖፕ ክሪል ተልኳል።
ይህ ውሳኔ ሁለተኛ አመቱን ሊይዝ የተቃረበው የሩሲያ- ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ፣ ቤተክርስቲያኗ በውስጧ ባሉ ተቃዋሚዎች ላይ እየወሰደች ያለው እርምጃ መጨመሩን የሚያሳይ እንደሆነ ተነግሯል።
የቤተክርስቲያኗ ፍርድ ቤት እንደገለጸው ቄስ ኡምንስኪይ ፖትሪያርክ ክሪል ተግባራዊ እንዲሆን ያዘዙትን ጸሎት ለማድረስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ የገቡትን ቃል ጥሰዋል።
"ተመልከት መዋጋት የሚፈልጉ በቅድስቲቷ ሩሲያ ላይ ጦር አንስተዋል፣ ለመከፋፈል እና አንድ የሆነውን ህዝቧን ለመስበር ተስፋ አድርገዋል" ይላሉ በፖትሪያርክ ክሪል እንዲደረስ የታዘዘው ጸሎት።
"ኦ እግዛብሔር ተነሳ፣ በኃይልህ ድል አቀዳጀን" የሚልም ተካቶበታል።
በደርዘን የሚቆጠሩ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቄሶች የቤተክርስቲያኗን አሰራር በመተቸታቸው ተባረዋል።
የኡምነስኪይ ኬሌሎቹ በተለየ ጉዳያቸው አነጋጋሪ የሆነው ከ30 አመታት በላይ በሞስኮ በማገልገላቸው እና ታዋቂ በመሆናቸው ነው።
በጽኑ ለታመሙ ህጻናት እና ልጆች የሚሆን ቦታ በማመቻቸት የሚታወቁት ኡምንስኪይ የቀድሞ የሶቬት ፕሬዝደንት ሚካኤል ጎርቫቼቭን የቀብር ስነ ስርአት መርተዋል።
ኡምንስኪይ ባለፈው ህዳር ወር በሰጡት ቃለ ምልልስ የጦርነት ቋንቋ ከቤተክርስቲያኗ ጋር አይሄድም ሲሉ ተናግረዋል።
ኡምነስኪይ ምዕመናን ከድል ይልቅ ሰላም የሚፈልጉ ቄሶችን እንዲከተሉ ያበረታቱ ነበር ተብሏል።
ዩክሬን መንግስትም በዩክሬን በሚገኙ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናት ላይ ማንገላታት በመፈጸም ክስ ሲቀርብበት ቆይቷል።