የሩሲያ ሰላይ ነው የሚባለው አሳ ነባሪ በጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፉ ተገለጸ
አሳ ነባሪው የተለያዩ ክፍሎቹ ላይ በጥይት መመታቱን የሚያሳዩ ምልክቶች ተገኝተዋል ተብሏል
ኖርዌይ በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ እነድታደርግ የእንስሳት መነብት ተቆርቋሪዎች ጠይቀዋል
የሩሲያ ሰላይ ነው የሚባለው አሳ ነባሪ በጥይት ተመቶ ህይወቱ ማለፉ ተገለጸ፡፡
ምዕራባዊያን ሀገራት ሩሲያ አሳ ነባሪን በማሰልጠን የአርክቲክ ሀገራትን እየሰለለች ነው ሲሉ ይደመጣል።
ሀገራቱ ይህንን እንዲሉ ያስቻላቸው ደግሞ ነጩ አሳ ነባሪ ሩሲያ ከኖርዌይ እና ስዊድን ጋር በምትዋሰንባቸው አካባቢዎች በመታየቱ ነበር።
ይህ አሳ ነባሪ በወገቡ ላይ ሰው ሰራሽ ቁስ መታየቱ፣ አሳ ነባሪው በተለየ መንገድ ለሰዎች ፍቅር ያለው መሆኑ የሩሲያ ሰላይ ነው እንዲባል ምክንያት ሆኗል።
ሩሲያ በበኩሏ አሳ ነባሪው ለስለላ ስራ ስልጠና በመስጠት አሰማርተዋለች መባሏን አስተባብላለች።
በአርክቲክ ውሀማ አካባቢዎች በተደጋጋሚ የሚታየው ይህ አሳ ነባሪ ምን አልባት ከእንስሳት መንከባከቢያ ስፍራ ያመለጠ ሊሆን እንደሚችል ግምቷን ተናግራለች።
ይሁንና ይህ ብዙ የተባለለት ነጩ አሳ ነባሪ ከአምስት ቀናት በፊት ሞቶ መገኘቱ አይዘነጋም፡፡
አሳ ነባሪውን በሩሲያ እና ኖርዌይ ባህር ላይ አሳ እያጠመዱ የነበሩ አባት እና ልጅ አግኝተውታል ተብሎም ነበር።
ጉዳዩ የብዙዎችን ትኩረት መሳቡን ተከትሎ የዚህ ተወዳጅ አሳ ነባሪ ሞት እንዴት ሊከሰት ቻለ የሚለው ጉዳይ ሲመረመር ቆይቷል፡፡
“የኩባ ንግስት” በመባል የምትታወቀው ሰላይ ከእስር ተለቀቀች
ዋን ሁዌል የተሰኘ የእንስሳት መብት አስከባሪ ድርጅት እንዳለው አሳ ነባሪው በጥይት ተመቶ መገደሉን የሚያሳዩ ምልክቶች እንደተገኙበት ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ድርጅቱ አክሎም አሳ ነባሪው ሞቶ የተገኘባት ኖርዌይ ወንጀሉ ለምን እና በማን እንደተፈጸመ ለማወቅ ምርመራ እንድታደርግ ጥያቄ ቀርቦላታል፡፡
ይህ አሳ ነባሪ ለሩሲያ ይሰልላል መባሉን ተከትሎ ህቫል የሚለውን የኖርዌይ ቋንቋ እንዲሁም የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስምን. በመውሰድ "ህቫልዲሚር" የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ነበር።