ዘለንስኪ ከትራምፕ ጋር ከተጋጩ በኋላ ዩክሬን ውስጥ ተቀባይነታቸው መጨመሩ ተገለጸ
የኪቭ አለምአቀፍ የሶሾሎጂ ኢንስቲትዩት ያካሄደው የህዝብ አስተያየት በመጋቢት ወር 67 በመቶ የሚሆኑ ዩክሬናውያን ዘለንስኪን ያምኑታል

ጥናቱ የተካሄደው ኪቭ ቁጥር አንድ ከሆነችው አሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በዋሽንግተን ኦቫል ኦፊስ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ቀውስ ውስጥ በገባበት ወቅት ነው
ዘለንስኪ ከትራምፕ ጋር ከተጋጩ በኋላ ዩክሬን ውስጥ ተቀባይነታቸው መጨመሩ ተገለጸ።
የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በኋይትሀውስ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ከተጋጩ ወዲህ በሀገር ውስጥ ያላቸው ተቀባይነት በ10 በመቶ ማደጉን ሮይተርስ የህዝብ አስተያየት በመሰብሰብ ቀዳሚ የሆነውን ተቋም ጠቅሶ ዘግቧል።
የኪቭ አለምአቀፍ የሶሾሎጂ ኢንስቲትዩት ያካሄደው የህዝብ አስተያየት በመጋቢት ወር 67 በመቶ የሚሆኑ ዩክሬናውያን ዘለንስኪን ያምኑታል።ይህ ጥናት የተካሄደው ኪቭ ቁጥር አንድ ከሆነችው አሜሪካ ጋር ያላት ግንኙነት በዋሽንግተን ኦቫል ኦፊስ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ቀውስ ውስጥ በገባበት ወቅት ነው።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶን ህሩሽትስካይ የህዝብ አስተያየቱ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ወታደራዊ ዘመቻ ከከፈተች ከሶስት አመታት በኋላ የዩክሬናውያን ከፕሬዝደንት ዘለንስኪ ጎን መሰለፋቸውን የሚያሳይ ነው ብለዋል።
"ዩክሬናውያን የአዲሱን የአሜሪካ አስተዳደር አካሄድ በዩክሬንና በዩክሬናውያን ላይ እንደተቃጣ ጥቃት አድርገው ያዩታል" ሲሉ ሁሩሽትስካይ ተናግረዋል። ሁሩሽትስካይ እንዳሉት ዩክሬናውያን ሰላም ይፈልጋሉ፤ በከፍተኛ ዋጋ የሚመጣ ሰላም ግን አይፈልጉም።
"የዩክሬናውያን ሰላም ይፈልጋሉ፤ ነገርግን ውጤታችን የሚያሳየው አብዛኞቹ የዩክሬናውያን ሰላም እንደማይፈልጉ ነው"ብለዋል ኃላፊው።
በ2ዐ19 የተመረጡት የ47ቱ የዩክሬን ፕሬዝደንት ዘለንስኪ ሩሲያ በየካቲት 2022 ልዩ ያለችውን ዘመቻ በዩክሬን ላይ ከከፈተች ወዲህ የጽናት ተምሳሌት ሆነዋል።
ከባለፈው የኋይትሀውስ ስብሰባ ወዲህ ፕሬዝደንት ትራምፕ "አምባገነን" ሲሉ የጠሯቸው ዘለንስኪ በዩክሬን ሰላም የማምጣት እቅዳቸው ላይ እንቅፋት እንደሆኑባቸው እየገለጹ ናቸው። አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገውን ወታደራዊ እርዳታ አቋርጣለች። ዘለንስኪ ኪቭ ከአሜሪካ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እየሞከረች እንደሆነ እየገለጹ ይገኛሉ።