ዩክሬን የሩሲያ ጦር ወደፊት እየገፋ መሆኑን አረጋግጣለች
የሩሲያ ጦር በምስራቅ ዩክሬን የሚገኙ ሁለት መንደሮችን መያዙን አስታወቀ።
ጦሩ በምስራቅ ዩክሬን ሰርባሪንካና ማይኪላይቭካ የተባሉ ሁለት መንደሮችን መቆጣጠሩን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የሩሲያ ጦር አሁን ላይ በአቅራቢያው የሚገኝ ከተማን ለመያዝ ወደፊት እየገፋ መሆኑንም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
የዩክሬን ጦር አካባቢዎቹ በሩሲያ ጦር እጅ ስለመውደቃቸው ማረጋገጫ ያልሰጠ ሲሆን፣ ሆኖም ግን በዙሪያው ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ስለመሆኑ አረጋግጧል።
በዩክሬ እና በዩክሬን በኩል ያሉ ብሎገሮች የሩሲያ ጦር በሴይልዶሽ ከተማ አቅራቢያ ከፍተኛ ውጊያ እያደረጉ እና ወደፊት እየገፉ ስለመሆናቸ አረጋግጠዋል ብሏል ሮይተርስ በዘገባው።
ከፍተኛ የዩክሬን ወታደራዊ አዛዥ በበኩላቸው፣ የዩክሬን ጦር በሰርባኒንካ አቅራቢያ 12 የሩሲያ ጦር ጥቃቶችን መቀልበሳቸውን አስታውቋል።
የሩሲያ ጦር ወደፊት እየገፋ መሆኑን ያረጋገጡት የዩክሬን ጦር አዛዥ፣ በፖክሮሶሽ ከተማ አቅራቢያ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ስለመሆኑ ገልጸዋል።
የሞስኮ ወታደሮች የዶምባስ ግዛትን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እየሞከሩ መሆኑ ይታወቃል።
የሩሲያ ኃይሎች የከሰል ማዕድን ወደሚወጣባት የምስራቅ ዩክሬኗ ሰሊዶቭ ከተማ በፍጥነት እየገሰገሱ መሆናቸውም ነው የተነገረው።
ዲፕ ስትቴት' የተባለው የክሬንን የግንባር ሁኔታ የሚገመግም የካርታ ፕሮጀክት የሩሲያ ኃይሎች የሰሊዶቭን ምስራቃዊ ጫፍ መቆጣጠራቸውን እና አብዛኛው የከተማዋ መሀል ክፍል የግጭት ቀጣና መሆኑን ያሳያል።
እንደ ኦፕን ሶርስ ዳታ ከሆነ ምንም እንኳን ዩክሬን የሩሲያን ኩርስክ ግዛት ብትይዝም፣ ፑቲን በፈረንጆቹ 2022 "ለልዩ ወታደራዊ ዘመቻ" ወደ ዩክሬን የላኳቸው ወታደሮች ከባለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በፍጥነት ወደፊት እየገሰገሱ ይገኛሉ።
ሩሲያ በ2014 የያዘቻትን ክሬሚያን ጨምሮ 1/5 የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት ይዛለች።