የባህረ ሰላጤውን ሃገራት በመጎብኘት ላይ ያሉት የሳዑዲ ልዑል አልጋወራሽ ዩኤኢ ገቡ
የአቡዳቢው ልዑል አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ተቀብለዋቸዋል
መሃመድ ቢን ሳልማን በኦማን የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው አቡዳቢ ገብተዋል
በተለያዩ የባህረ ሰላጤው (ገልፍ) ሃገራት ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የሳዑዲ አረቢያ ልዑል አልጋወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን አቡዳቢ ገቡ፡፡
መሃመድ ቢን ሳልማን በኦማን የነበራቸውን ጉብኝት አጠናቀው ነው አቡዳቢ የገቡት፡፡
የአቡዳቢው ልዑል አልጋወራሽ እና የዩኤኢ ጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንም ተቀብለዋቸዋል፡፡
የልዑል አልጋወራሹ ጉብኝት የሁለቱን ሃገራት ወንድማዊ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል ተብሏል፡፡
ልዑል አልጋወራሾቹ በ7 ወራት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ሲገናኙ፡፡ ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ባሳለፍነው ወርሃ ሃምሌ እና ግንቦት በሳዑዲ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
ሳዑዲ እና ዩኤኢ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውንና ትብብራቸውን ለማጠናከር በፈረረንጆቹ 2016 የጋራ ምክር ቤት መስርተዋል፡፡
የዩኤኢ የደህንነት አማካሪ በኢራን ጉብኝት አካሄዱ
በወርሃ ግንቦቱ የሼክ መሃመድ የሪያድ ጉብኝት ፓርላሜንታዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውም የሚታወስ ነው፡፡
የገልፍ ጉብኝታቸውን ትናንት ሰኞ የጀመሩት ልዑል አልጋወራሹ በኦማን መስካት በነበራቸው ቆይታ በተለያዩ የሁለትዮሽ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ከሃገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል፤ 13 የሚጠጉ ስምምነቶችንም አድርገዋል፡፡
መሐመድ ቢን ሳልማን የሳዑዲ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የመከላከያ ሚኒስትርም ናቸው፡፡