የሳዑዲ ንጉስ ልጃቸው ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማንን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ
ንጉሱ ሁለተኛው ልጃቸው ልኡል ካሊድን የመከላከያ ሚኒስቴር አድርገው ሾመዋል
ንጉሱ ሁለተኛው ልጃቸው ልኡል ካሊድን የመከላከያ ሚኒስቴር አድርገው ሾመዋል
የሳዑዲ አረቢያ ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱላዚዝ ልጃቸው ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሰልማንን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን አስታውቀዋል።
ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱላዚዝ ባካሄዱት የካቢኔ ሹም ሽር ሁለተኛ ልጃቸው ልኡል ካሊድን የመከላከያ ሚኒስቴር አድርገው መሾማቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ንጉሱ ሌላኛለው ልጃቸው ልዑል አብዱላዚዝ ቢን ሳልማንን ደግሞ የኢነርጂ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውን ባወጡት ንጉሳዊ አዋጅ አስታውቀዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልኡል ፋይሰል አል-ሳዑድ፣ የፋይናነስ ሚኒስትር ሞሃመድ አል ጃዳን እና የኢንቨስትመንት ሚኒስትር ካሊድ አል ፋሊህ በያዙት ኃፊነት መቀጠላቸውን ንጉሳዊ አዋጁ አመላክቷል።
ሳዑዲን እንደቀየሩ የሚነገርላቸው ልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ከመከላከያ ሚኒስትርነት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሸጋገሩ ሲሆን፤ ግዙፏ የነዳጅ ላኪ የሆነቸው የሳዑዲ አረቢያ መሪነት በቀዳሚ ሚነሱ ናቸው።
አዲሱ የልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን የጠቅላይ ሚንስትርነት ሚና ንጉሱ ከቀድሞው ተልእኮ ጋር የሚሄድ ሲሆን በውጪ ጉብኝቶች ሀገሪቱን በመወከል መጓዝ እና በግዛቱ የሚስተናገዱትን የመሪዎች ጉባኤዎችን በሊቀ መንበርነት መምራትን ያካትታል።
የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት የልዑል አልጋ ወራሽ መሃመድ ቢን ሳልማን ታናሽ ወንደም ልኡል ካሊድ ከዚህ ከደም የመከላከያ ሚኒስትር ደኤታ በመሆን ያገለገሉ ነበር ተብሏል።
የሳዑዲ ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱላዚዝ የሚገኙባቸውን የካቢኔ ስብሰባዎች አሁንም በመምራት እንደሚቀጥሉ የንጉሳዉያን አዋጁ አመላክቷል።
የ86 ዓመቱ ንጉስ ሳልማን ለሁለት ዓመት ከግማሽ ያክል ልዑል አላጋ ወራሽ ሆነው ከቆዩ በኋላ የሳዑዲ ንጉስ በመሆን በፈረንጆቹ 2015 በትረ ስልጣኑን መቆጣጠራቸው ይታወሳል።
ንጉስ ሰልማን ቢን አብዱላዚዝ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በተለያዩ የጤና እክሎች በተደጋጋሚ ሆስፒታል ገብተው እንደነበረም አይዘነጋም።