ፖለቲካ
በሳዑዲ የሚመራው ጥምር ጦር በረመዳን ወር የተኩስ አቁም ማወጁን አስታወቀ
ከፈረንጆቹ 2015 ወዲህ በሳዑዲ በሚመራው ጥምር ጦርና በሆውሲ አማጽያን መካከል ጦርነት ሲካሄድ ቆይቷል
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዓለም አቀፉማህበረሰብ በየመን ሰላምን ለማምጣት እያደረገ ለነበረው ጥረት ተስፋ ሰጪ እርምጃ ነው
በየመን ውስጥ ከሆውሲ አማጽያን ጋር እየተዋጋ ያለው በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጦር የረመዳን ወርን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ማወጁን አስታወቀ።
ጦሩ ከውሳኔው ላይ የደረሰው ታላቁ የረመዳን የጾም ወር መቃረቡን ተከትሎ ተመድ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ነው።
- በሃውሲ አማጽያን የተመለመሉ 2 ሺ ህጻናት በየመን ጦርነት ሞተዋል- ተመድ
- ሳዑዲ የየመን ጦርነት እንዲያበቃ እስከ ተኩስ አቁም የሚደርስ የስምምነት ሃሳብ አቀረበች
በዚህም መሰረት በሳዑዲ የሚመራው ጥምር ጦር ትናንት ባወጣው መግለጫ ከዛሬ ጀምሮ በየመን የተኩስ አቁም ማድረጉን አስታውቋ
ተመድ በየመን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በፈረንጆቹ 2015 ከተጀመረ ወዲህ በሳዑዲ ከሚመራው ጥምር ጦር እና በኢራን እንደሚደገፍ ከሚነገርለት የሆውሲ አማጽያን ጋር ሰላምን ማምጣት በሚቻልበት ላይ ተቀራርቦ ሲሰራ ቆይቷል።
አሁን ላይ የረመዳን ወርን ተከትሎ የተደረሰው የተኩስ አቁም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ላለፉት 3 ዓመታት በሀገሪቱ ሰላምን ለማምጣት ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያደረገ ለነበረው ጥረት ተስፋ ሰጪ እርምጃ እንደሆነ ተነግሯል።