የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት የሚያደርጉትን ጥረት አሜሪካ እንደምትደግፍ ገለፀች
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር ተወያይተዋል
የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ከኢትዮጵያ ም/ጠ/ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋርም ተወያይተዋል
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር አንቶኒ ብሊንከን በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋር መወያየታቸውን አስታውቀዋል።
በውይይታቸውም የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር አንቶኒ ብሊንከን የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን ለማሸማገል የሚያደርጉትን ጥረት አሜሪካ እንደመትደግፍ ገልፀዋል።
አንቶኒ ብሊንከን እና ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በውይይታው በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት እየተሳተፉ ያሉ ሁሉማ አካላት ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በአስቸኳይ ማቆም በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።
እንዲሁም በቶርነቱ እየተሳረፉ ያሉ አካላት ያለ ቅድመ ምንም ሁኔታ ወደ ተኩስ አቁም እንደሚጡ ማስቻል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ ላለው ቀውስ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝለት እያደረጉት ያለውን ጥረት አሜሪካ አውቅና እንደምትሰጠውም ብሊንከን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።
የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር አንቶኒ ብሊንከን አክለውም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸውንም አስታውቀዋል።
በውይይታው ወቀትም ኢትዮጵያውያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማስጠብቅና ሰላም ለማምጣጥ የሚወሰዱ ተጨባጭ ዕርምጃዎችን አሜሪካ እንደመትደግፍ ገልፀዋል።